“አባ ቶርቤ’’ በሚል ስያሜ ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተያዙ

68

ግንቦት 29/2011 በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድብቅ ጥቃት ይፈጽማል የሚባለው “አባ ቶርቤ” የተሰኘ ቡድን አባላት በቡራዩ ተያዙ።   

“አባ ቶርቤ’’ ወይም "ባለሳምንት" በሚል ስያሜ በድብቅ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጥቃትና ወንጀሎችን በመፈጸም የተጠረጠሩ ግለሰቦች ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽንቢሮለኢዜአእንደገለጸው፤ በጸጥታ አካላት ክትትል በነፍስ ግድያ እና የተለያዩ ወንጀሎችን በማቀነባበርና በመፈጸም የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት በቡራዩ ከተማ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ማምሻውን በጋራ ተከራይተው በቆዩበትቤት በቁጥጥር ሥር ሲውሉ አራት ማዳበሪያ የመከላከያ ሠራዊት አልባሳት እና ሌሎች ቁሳቁሶች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ለኢዜአ ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም