የአፍሪካ ህብረት የፀጥታው ምክር ቤት ሱዳንን ከህብረቱ አባልነት አገደ

44

ግንቦት 29/2011 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሱዳንን ከህብረቱ አባልነት አግዷል።

የሱዳን ወታደሮች በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ ከመቶ ሰዎች በላይ እንደሞቱ እና ከ500 ሰዎች በላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው እየተነገረ ነው፡፡

የአገሪቱ መንግስት እስከ አሁን የሟቾች ቁጥር ከ61 እንደማይበልጡ ነው በጤና ጥበቃው ሚኒስቴር በኩል ያስታወቀው፡፡

ዛሬ በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ የመከረው የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ሱዳንን ከህብረቱ አባልነት ያገደ ሲሆን እገዳው በአገሪቱ የሲቪል መንግስት እስኪቋቋም ድረስ የፀና ይሆናል ተብሏል።

ምክር ቤቱ በአገሪቱ አሁን ካለው ሁኔታ ብቸኛው መውጫ መንገድ የሲቪል መንግስት ማቋቋም ነው ማለቱን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም