መምህራን ለብሄራዊና ክልል አቀፍ ፈተናዎች ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

49

ግንቦት 29/2011 መምህራን በክልልና አገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጥሪ አቀረበ። 

ማህበሩ በደብረ ማርቆስና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ላይ የደረሰውን ሞትና የአካል ጉዳት አውግዟል።

ማህበሩ አገር አቀፍና ክልልአቀፍ ፈተናዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንትዶክተር ዮሐንስ በንቲ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ከሰኔ 3 ቀን እስከ ሰኔ 14 ለሚሰጡት አገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፈተናዎችየተመለመሉ ፈታኞች፣ ተቆጣጣሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው።

ፈተናዎቹ በስኬት እንዲጠናቀቁማህበሩ የሚሳተፍበት ኮሚቴ በየክልሉ መዋቀሩንና በኮሚቴው ውስጥ ማህበሩ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑንም ተናግረዋል።

የፈተናዎቹ ውጤት የመምህራን የድካም ውጤት ጭምር በመሆናቸው የማህበሩ አባላት ለፈተናዎቹ በስኬት መጠናቀቅ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ማህበሩ በደብረማርቆስና በአክሱምዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ላይ በደረሰው የሞትና የአካል ጉዳት ማዘኑን ገልፀው ማህበሩ ይህንን ተግባር ያወግዛል ብለዋል።

ተማሪዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፃኢእድላቸው ወሳኝ መሆኑን ተገንዝበው መተባበር እንዳለባቸውና የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን እርምጃ መውሰድ እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ በየአካባቢው ያለው የትምህርት ማህበረሰብም ለሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደቱ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩል ማህበሩ ባለፉት 70 አመታት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መምህራንን የማስተባበርና የመምህራንንህጋዊ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የተለያየየ ተግባራትን ሲያከናውን እንደነበር አብራርተዋል።

የመምህራንን ጥቅማጥቅም ለማስከበርባከናወናቸው ተግባራት የመምህራን የደረጃ እድገት እርከን ማሻሻያና ያለባቸውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት የመኖሪያ ቤት ፓኬጅ በመቅረፅ ከ55 ሺህ በላይ መምህራን የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታ ተደርጓልም ብለዋል።

እነዚህ ጥያቄዎች መመለስ ቢጀምሩም አፈፃፀማቸው በመጓተቱ በታችኛው የመንግስት እርከን የሚገኙ አመራሮች ለጉዳዩ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡም ጠይቀዋል።  

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ አባላት እንዳሉትም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም