ቀዳማዊት እመቤት በዋግ ኽምራ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊያስገነቡ ነው

203

ግንቦት 29/2011 ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በነገው እለት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ ያስቀምጣሉ።

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማስገንባት በነገው እለት የመሰረት ድንጋይ  እንደሚያስቀምጡ የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ሃላፊ አቶ ሽታው አዳነ ለኢዜአ እንደገለፁት ቀዳማዊት እመቤት  የሚያስገነቡት ትምህርት ቤት በአካባቢው የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ተቋም እንደሌለ  እና  የአካባቢው ተማሪዎች ወደ ተለያዩ ትምህርት ቤቶች በእግር ተጉዘው እንደሚማሩ  ተናግረዋል፡፡

“የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ መገንባታ  ተማሪዎች እንግልት ሳይገጥማቸው  በአካባቢያቸው ትምህርት እንዲያገኙ ከማስቻሉም ባለፈ ለትምህርት ሽፋኑ ከፍተኛ  አስተዋፅኦ አለው” ብለዋል፡፡

በነገው እለት ከቀዳማዊት እመቤቷ በተጨማሪ የክልል እና የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች  ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በፈፋ ቀበሌ ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ያሉ ሲሆን ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በመንደር ማሰባሰብ ስርዓት መኖር እንደጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም