የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድርቅ ምክንያት ለተፈናቀሉ ሶማሊያውያን ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ

135

ግንቦት 28/2011 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ማህበረሰብ በድርቅ ምክንያት ለተፈናቀሉ ሶማሊያውያን  ድጋፍ እንያዲደርግ ጥሪ አቀረበ።

በተበበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ 2 ሚሊዮን ሶማሊያውያን የምግብ እርዳታ ይሻሉ ማለቱን ሲጂቲኤን ዘግቧል።  

ኤጀንሲው የአለም የአካባቢ  ቀንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው  የምስራቅ አፍሪካዋ አገር ሶማሊያ በድርቅ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ዜጎቿ ከዓለም ማህበረሰብ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋታል፡፡


ሁሉም ዓይነት የህግ ማዕቀፎችን ተግባራዊ በማድረግ ከአየር ንብረት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ  አደጋዎችን መከላከል እና በተለይም የአለም ህዝብ የአየር ንብረት ለውጥ ከሚያስከትለው ጉዳት ለመታደግ የሚያስችል ዓለማቀፋዊ ጥረት እንዲደረግ ኤጀንሲው ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሶማሊያ እአአ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ 2018 እንዲሁም ከሚያዚያ አስከ ሰኔ - 2019 በነበረው ዝቅተኛ  የዝናብ መጠን  በበርካታ የሃገሪቱ አካባቢዎች ድርቅ እንዲከሰት አድርጓል ተብለዋል፡፡


እንደ ድርጅቱ መረጃ እአአ እስከ ሀምሌ 2019 ባለው ግዜ 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሶማሊያውያን የምግብ ዋስተናቸው የማይረጋገጥ ሲሆን 2.2 ሚሊዮን ህዝብ ደግሞ አስቸካይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ነው የሚያሳየው፡፡

የእርዳታ ድርጅቶች በበኩላቸው 710 ሚሊዮን ዶላር በመሰብሰብ 4.5 ሚሊዮን በድርቅ ተጎጂ የሆኑ ዜጎችን ለመደገፍ የድርቅ ምላሽ መርሃ ግብር አውጥተው እየሰሩ እንደሆነም ተገልጿል።
በድርቁ ምክንያትም እስከ አሁን በአብዛኛው ከከተማው  የአገሪቱ አከባቢ  ውሃ እና ምግብ ፍለጋ 49 ሺ የሚሆን ህዝብ ከቀየው ተፈናቅሎ ተሰድደዋል፡፡

ሶስቱ የሶማሊያ ዋና ዋና ክልሎች ማለትም ደቡብ ማዕከላዊ፣ ፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ በዝቅተኛ የዝናብ መጠን እና አልፎ አልፎ በሚከሰተው ድርቅ ችግር ውስጥ መግባታቸውን የዘገበው ሲጂቲኤን አፍሪካ ነው።   

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም