የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ተጀመረ

67

ግንቦት 28/ 2011 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ከጀርመንና ደቡብ አፍሪካ በመጡ ባለሙያዎች እየተሰጠ ነው። 
ስልጠናውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር፣ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና ከምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ማህበር ጋር በመሆን አዘጋጅቶታል።

ዛሬ የተጀመረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እየተሰጠ ነው።

በመጀመሪያ ዙር ስልጠና የሁለተኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ሰርተፍኬት ያላቸው የአጭር ርቀት ፣ የውርወራ፣ የዝላይ፣ የመሰናክል ሩጫና  የእርምጃ ውድድር  አሰልጣኞች  ይካፈላሉ።

በሁለተኛው ዙር በረጅምና መካከለኛ ርቀት  የሚያሰለጥኑና  የአንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ፈቃድ ላላቸው ባለሙያዎች የሚሰጥ እንደሆነ ተነግሯል።

ስልጠናው ቀደም ሲል በተለይም በአጭር ርቀትና በሜዳ ላይ ተግባራት የሚስተዋለውን የአሰልጣኞች የአቅም ማነስ ችግር ለመፍታት ይረዳል ነው የተባለው።

በተግባርና በንድፈ ሀሰብ ታግዞ በሚሰጠውና ለ16 ቀናት በሚዘልቀው የሁለት ዙሮች ስልጠና በድምሩ 20 አሰልጣኞች ይሳተፉበታል።   

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም