በድሬዳዋ ሆነ በአገር የተጀመሩ የሰላምና የልማት ተግባራት ለማጠናከር እንሰራለን-አስተያየት ሰጪዎች

83

ድሬዳዋ ግንቦት 28/ 2011 በረመዳን ፆም ወር የተጀመሩ የእርቅና የአንድነት ተግባራትን በማጠናከር የአካባቢያቸውን ሰላምና አገራዊውን ለውጥ ዳር ለማድረስ እንደሚተጉ የድሬዳዋ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተናገሩ። 

አስተያየት ሰጪዎች ይህን የተናገሩት ትናንት 1440ኛውን የኢድ አልፈጥርን በዓል በደመቀ የሶላት ሥነ-ሥርዓት ባከበሩበት ወቅት ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት ነው፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ ገለፃ በግልም ሆነ በጋራ በኃይማኖትና በብሔር ሳይለያዩ ሰላምን ለማስፈንና ልማቱን በማጠናከር ጠንክረው ይሰራሉ፡፡  

በሶላት ላይ የተሳተፉት አቶ ሙስጠፋ በያን የዘንድሮ ረመዳን በከተማዋ የእርቅ ፣የፍቅር፣የአንድነት መንፈስ እንዲሰፍን ምክንያት የሆነ ወር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በበዓሉም እነዚህን ተግባራት ለማጠናከር የድሬዳዋን ህብረትና ፍቅር በማጠናከር የተጀመረውን ልማት ለማስቀጠል እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

በብሔር ተቧድኖ የመጋጨትና በኃይማኖት ተከፋፍሎ የመገፋፋት መንፈስ የድሬዳዋ መገለጫ አለመሆኑን የገለፁት ደግሞ አቶ አብዱልሃፊዝ ሻፊ ናቸው፡፡

ነዋሪዎቿ በኅዘንና በደስታ የማይለያዩ ፣በልዩነት ውስጥ ልዩ የጋራ እሴት የገነቡ በመሆናቸው እሴቶች በመጠበቅ የሰላም፣ የልማትና የአንድነት ጉዞ ማጠናከርና አገራዊ ለውጡን በማራመድ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡

''እኔወጣቶችን የኛ ዘመን የፍቅርና የአንድነት ታሪክ እያስተማርኩ ነው። አዲሱ ትውልድ ወደ ፍቅርና ሰላም ለማምጣት ማስተማር ይገባል'' ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ወይዘሮ ኑጁማ መሐመድ የተባሉ ነዋሪ በበኩላቸው በረመዳን ፆም ወቅት ወጣቶች እርስ በርሳቸው ፈቅደው ወደ ፍቅር መንገድ መመለሳቸው እንዳስደሰታቸው ይገልጻሉ። 

ይህምየተጀመረውን የሰላም ጉዞ ለማስቀጠል ኃላፊነታችን እንድንወጣ አነቃቅቶናል ብለዋል፡፡

''እናቶች ለአካባቢው ሰላም መጠበቅ፣ ለተሰሩ ልማቶችን መጠናከር ማህበር ፈጥረን እየሰራን እንገኛለን'' በማለትም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ወጣት አዲል ዩኒስ በከተማው አንዳንድ ቀበሌዎች ወጣቶች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች እንደማይፈቱአድርገው የሚናገሩአካላትን ያሳፈረ እርቅ ተፈጥሮ ወጣቶች በብሔር ፣በኃይማኖትና በጎሳ ሣይለያዩ በልማትና በሰላም ማስፈንተግባራትግንባር ቀደም ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ናቸው ይላል፡፡

ሌላዋ ወጣት ሳፊያ አህመድ በረመዳን ፆም ያለው የፍቅርና የመማማርተግባራት ምንጊዜም መቀጠል እንዳለበት ትናገራለች፡፡

የድሬዳዋ አመራሮች፣ የወጣቶች ችግሮች እስከ ታች በመውረድ ችግሮችን በየጊዜው በመለየትና መፍትሄ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቃለች፡፡

ወጣት ኢማን አሊ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥና የአካባቢውን ሰላም የሚያደፈርሱ፤ ኃይማኖትና ብሔርንበመጠለል ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ አካላትን እየተከላከሉ መሆናቸውን ገልጿል።

በወንጀል የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችንም ለፍትህ አካላት እየሰጠን እንገኛለን ብሏል፡፡

''መንግሥት የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ኃላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ። እኛ የራሳችንን ኃላፊነትን እንወጣለን። እንዲህ ከሆነ ሰላም፣ ፍቅርና ልማታችን ይመለሳል''ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም