1440ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል በኦሮሚያ ደረጃ በቡራዩ ከተማ በድምቀት ተከበረ

68

ግንቦት 27/2011 በኦሮሚያ ደረጃ በቡራዩ ከተማ በተከበረው 1440ኛ የኢድ አል ፈጥር በዓል ሶላት ፕሮግራም በኋላ በተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች ለህዝበ ሙስሊሙ የምሳ ግብዣ ተደርጓል።

በምሳ ግብዣው ላይ የክርስትናየዋቄፈታ እምነት አባቶች፣የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊች፣የኦ ኤም ኤን ዳይሬክተር አቶ ጀዋር መሀመድ፣የቡራዩ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰለሞን ፈዬ  እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችም ተገኝተዋል።

 በተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች፣በአባገዳዮችናየአገር ሽማግሌዎች ለሙስሊም ወንድሞቻቸው ያዘጋጁት የምሳ ግብዣ በጣም እንደስደስተቻውና አንድነትና ወንድማማችነትን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ህዝበ ሙስሊሙም ገልጸዋል።

በዓሉ የደስታ እንደመሆኑም ሁሉም ሰው ተደስቶ የሚውልበት ቀን ላይ በመሆኑ ህዝቡ ተሳስቦ፣ተፈቃቅሮናያለው ለሌላቸው በማካፈል፣በመረዳዳት የሚውል ነው ሲሉም የእምነቱ ተከታዎች ተናግረዋል።

እንዲህ ዓይነት አብሮነት መተሳሰብና መፈቃቀር ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን ያሉት ተሳታፊዎቹ፤እንዲህ አይነት የአንድነት ተግባራትን በዘላቂነት በማጠናከርና በመንከባከብ የበለጠ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

በምሳ ግብዣ ላይ የተገኙት የኦርቶዶክስና የዋቄፈታ እምነት ተከታዎች በበኩላቸው ሁሉም የሰው ዘር አንድ በመሆኑ የሙስሊም ወንድሞቻችን በዓል አብሮ ለማክበር እና አብሮ ለመደሰት መገኘታቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የህዝበ ሙስሊም ጥያቄ መመለሱና እንድነታቸው መጠናከሩ፣በዓሉ በሰላምና በፍቅር መከበሩ፣ ከኢድ በፊት የመስኪድ አካባቢ በተለያዩ እምነት ተከታዮች ጽዳት መካሄዱ የዘንድሮን የኢድ በዓል ልዩ ያደርገዋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሙስሊምና በሌሎች እምነት ተከታዮች መካከል የበለጠ አንድነትና መተሳሰብ የተጠናከረበት  በዓል በመሆኑና ህዝበ ሙስሊሙ ለዘመናት ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ ልዩ በዓል እያከበርን ነው ብለዋል።

በቀጣይም ሁሉም ህብረተሰብ በአንድነትና በመተባበር ወደ ልማት ስራ መግባት አለበት ብለዋል አቶ ሽመልስ።

1440ኛ የኢድ አል ፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ እየተከበር ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም