የክልሉ ዓመታዊ ቦክስ ሻምፒዮና ተጀመረ

70

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዓመታዊ የቦክስ ሻምፒዮና ዛሬ በአሶሳ ተጀመረ፡፡

አሶሳ ግንቦት 26 / 2011  በውድድሩ የዳንጉር ወረዳ፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደርና በአስተዳደሩ ስር የሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ይሳተፋሉ፡፡

ውድድሩ በሁለቱም ጾታዎች ከ45 ኪሎ ግራም እስከ 75 ኪሎ ግራም እንደሚካሄድ በክልሉ ስፖርት ኮሚሽን የቦክስና ክብደት ማንሳት ፌዴሬሽን ጸሐፊ አቶ ለዓለም ጥላሁን ገልጸዋል፡፡

ውድድሩ በቅርቡ አገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ውድድር ክልሉን የሚወክሉ ምርጥ ስፖርተኞችን ለማፍራት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በኮሚሽኑ የስፖርት ስልጠናና ውድድር የኅብረተሰብ ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ አጠይብ መሐመድ ታዳሚዎች ውድድሩን በስፖርታዊ ጨዋነት በመከታተል ለስፖርቱ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በመክፈቻ  በተደረገው ውድድር በ56 ኪሎ ግራም ምድብ አሶሳ ከተማ ወረዳ 02 ዳንጉር ወረዳን 74 ለ 69 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ውድድሩ እስከ ግንቦት 28 / 2011 እንደሚካሄድ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም