ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሰንበት ተማሪዎች ጋር በመሆን የኢድ አልፈጥር በዓል የሚከበርበትን ስፍራ አጸዱ

81

አዲስ አበባ  ግንቦት 26/2011 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ተማሪዎች ጋር በመሆን የኢድ አልፈጥር በዓል የሚከበርበትን የአዲስ አበባ ስታዲየምና አካባቢውን ዛሬ አጽድተዋል።

በመላው የእስልም እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የኢድ አልፈጥር በዓል ኢድ ሶላት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይከበራል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን የሰንበት ተማሪዎች ጋር በመሆን አካባቢውን አጽድተዋል።

የሙስሊም ወንድምና እህቶችን የረመዳንወር ፆም ማብቂያአስመልክቶየክርስትና እምነት ተከታዮች አጋርነታቸውን የበዓሉን ማክበሪያ ስፍራ በማጽዳትአሳይተዋል።

የከተማዋ ወጣቶችም የኢድ ሶላት የሚከናወንበትን ስታዲየም በጋራ ማጽዳታቸውን  የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በድረ-ገጹ አስፍሯል።

ካለፈው ዓርብ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የአምልኮና የኢድ ሶላት መስገጃ ስፍራዎችን ሲያፀዱ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም