ዓለም አቀፍ የውሃ ልማት ሲምፖዚየም በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሊካሄድ ነው

114
አርባምንጭ ግንቦት 30/2010 18ኛው ዓለም አቀፍ የውሃ ልማት ሲምፖዚየም  በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ዩኒቨርስቲው አስታወቀ፡፡ የዩኒቨርስቲው ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ በቀለ ለኢዜአ እንደገለጹት "የውሃ ሀብታችን ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው ሲምፖዚየም  በውሃ ሀብቶች ላይ የተካሄዱ 22 ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ። በውሃ ምህንድስናና ምርምር የካበተ ልምድ ያላቸው የአስር ሀገር ዩኒቨርስቲዎች ተሞክሮ እንደሚያቀርቡም ተመልክቷል። አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በውሃው መስክ በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ያለውን ራዕይ ለማሳካት ተቋሙ በየዓመቱ በሚያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም  ልምድ እያገኘ መምጣቱን ገልጸዋል። ለሁለት ቀን በሚቆየው  ሲምፖዚየም ውሃ በድህነት ቅነሳ ባለው ፋይዳ ላይ ይበልጥ እንደሚያተኩር አቶ ፍሰሃ ጠቁሟል። የውሃ ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች በሲምፖዚየሙ እንደሚሳተፉም ይጠበቃል፡፡              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም