ከ16 ዓመት ልጃገረድ ሆድ ግዙፍ የተቋጠረ ፀጉር ተወገደ

126

ግንቦት 22/2011 ከ 10 አመት በኋላ ከ16 አመት ልጃገረድ ሆድ የተወገደው ግዙፍ የተጠቀለለ ፀጉር የራሷ ፀጉር እንደሆነ ዘ ሚረር በድረ-ገጹ አስነብቧል።

ልጅቷ  ቀዶ ጥገና ከተደረገላት በኋላ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለች ተዘግቧል።

ከሆዷ ፀጉር የተወገደላት ልጅ በራምፕዘል ሲንደረም በሽታ የተጠቃች ስትሆን ይህ ዓይነቱ ችግር ያለባቸው ሰዎች የራስ ፀጉር የማኘክ ሱስ ተጠቂ እንደሚያደርጋቸው በመረጃው ሰፍሯል።

ለአስርት ዓመታት ሆዷ ውስጥ ተከማችቶ የነበረው  ፀጉር ስሰበሰብ  ግማሽ ኪሎ ግራም ክብደት እንዳለውም ተዘግቧል።

የሩስያውቷ ልጃ ገረድ በሳይቤሪያ ቶምስክ ከተማ ድንገተኛ የሆነ ቀዶጥገና በማድርግ ነው የፀጉር ጥቅልሉን ማውጣት የቻሉት።

የሕክምና ባለሙያዎች 80 በመቶ  የልጅቷ ሆድ ግዙፍ በሆነው የተጠቀለለ ፀጉር ምክንያት  ከጥቅም ወጭ ሆኖ እንደነበርም ተናግረዋል።

ጨጓራዋ ላይ  ሙሉ በሙሉ  የመዝጋት አደጋ ተደቅኖባት እንደነበር የሆስፒታሉ ዶክተር አንድሬ ካርቫቭ ገልፀዋል።

እንደ ሪፖርቱ ገለፃ ቀዶ ጥገናው በቶምሲክ በሚገኘው የድንገተኛ መድኃኒት ክሊኒክ ቁጥር ሁለት አስቸኳይ እንደታየ በመረጃው ሰፍሯል።

በአከባቢው እንዲህ አይነቱ የራምፕዘል ሲንደረም በሽታ ከ25 አመት በኋላ ሲከሰት ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነ በሪፖርቱ ተገልፅዋል።  

ልጅቷ የስነአእምሮ ሕክምና ክትትል ማድርግ እንዳለባትም ዶክተሮች ተናግረዋል።

ፀጉሩ በሆዷ ውስጥ ሊከማች  የቻለው የሰው ልጅ ጨጓራ ፀጉር መፍጨት ስለማይችል እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ገልፀዋል።

የተጠቀለለው ፀጉር ሆዷ ውስጥ እንዳለ ሐኪሞች  ከማወቃቸው  በፊት  ልጅቷ ፀጉሬን አጣሁት በማለት ተናግራ እንደነበር ሚረር ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም