ኢትዮጵያና ኩባ የሁለትዮሽ ግኑኝነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

93

አዲስ አበበባ ግንቦት 21/2011 ኢትዮጵያና ኩባ የሁለትዮሽ ግንኙነተታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ። 

የኩባው ምክትል ፕሬዚዳንት ሳልዶር አንቶኒዮናምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ያካሄዱት ውይይትየአገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

ሁለቱ አገራት በጤና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂና በትምህርትመስክች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ መክረዋል።

የሁለቱ አገራት ግንኙነት 'በደምና ባአጥንት የተሳሰረና የጠነከረ ነው' ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ግንኙነቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በውይይታቸውበስኳር ልማት የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትብብር ለማድረግም ተሰማምተዋል።

የኩባው ምክትል ፕሬዚዳንት ሳልቫዶር በበኩላቸው ውይይቱ የሁለቱን አገራት የቆየና የጠነከረ ግንኙነት ለማስፋትና ለማጎልበት ያለመና 'ስኬታማ ነበር' ብለዋል።

የኩባው ምክትል ፕሬዚዳንት ሳልቫዶር አንቶኒዮ ቫልዴስ ሜሳ፣ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ጎንዛሌዝ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ አማካሪ ብርጋዴር ጀኔራል ኤርናልዶ ታማዮ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ቢሮ በተካሄደው ውይይት የኢትዮጵያ የሳይንስናየከፍተኛትምህርት፣የኢኖቬሽንናቴክኖሎጂእና የጤና ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዴኤታዎች ተገኝተውበታል።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም