የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ነገ ይካሔዳል

60

ግንቦት 21/2011 የቤኒንሻጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አራተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በነገው ዕለት እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ።

የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ አቶ ሃብታሙ ታዬ ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ምክር ቤቱ ነገ በአሶሳ ከተማ 5ኛ ዓመት 4ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡

ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ የምክር ቤቱ ዋነኛ መወያያ አጃንዳ እንደሆነ አመልክተው ሌሎች ጉዳዮችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በ2011 በጀት ዓመት አስቸኳይ ጉባኤ ሲያካሂድ የነገው ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም