ብጹ አቡነ ኤልሳ ኪዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

101

ግንቦት 18/2011 የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብት ሊቀ-ጳጳስ ብጹ አቡነ ኤልሳ ኪዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
የዞኑ ሀገረ ስብከት ለኢዜአ እንዳስታወቀው ሊቀጳጳሰ አቡነ ኤልሳ ላለፉት 42 ዓመታት በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ያገለገሉ ታላቅ አባት ነበሩ፡፡

ብጹዕነታቸው ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ በከፋ፣ በደቡብና በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከትቶች በሊቀ-ጳጳስነት አገልግለዋል።

በጠቅላይ ቤተክህነት ቅዱስ ሲኖዶስም ለብዙ ዓመታት በዋና ጸሐፊነትና የካህናት አስተዳደር መምሪያ ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል ፡፡

በአርባ ምንጭ በመጽሃፍና በቅዳሴ መምህርነት እንዲሁም በደብረጽጌ ታላቁ ገዳም የፍትሃ ነገስትና የድጓ መምህርም ነበሩ።

ብጹ አቡነ ኤልሳ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ84 ዓመታቸው ትላንት ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ።

የቀብራቸው ስነስርአት የትውልድ ስፍራቸው በሆነው በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ ቤተ-ክርስቲያን ግንቦት 20 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚፈጸም ተመልክቷል።

በነገው እለትም በጎንደር ከተማ መስቀል አደባባይ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ ለአስከሬናቸው ስርአተ ፍታትና የሽኝት ስነስርአት እንደሚከናወን የሀገረ ስብከቱ ጽህፈት ቤት ስራአስኪያጅ አባ ዮሴፍ ደስታ አስታውቀዋል፡፡

የጠቅላይ ቤተክህነት አባቶች፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ፓትርያርኩ በተገኙበት ስርዓተ ቀብራቸው እንደሚፈፀምም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም