የአፍሪካ ቀን በኢትዮጵያ እየተከበረ ነው

67

አዲስ አበባ ግንቦት 17/2011 የአፍሪካ ቀን በኢትዮጵያ እየተከበረ ነው

"የአፍሪካ ቀን"የአፍሪካን መራራ የነፃነት ትግልና ብሩህ ተስፋ በማሰብ የሚከበር ሲሆን፤ አፍሪካውያን ባህላቸውን፣ ትውፊታቸውን እና ስልጣኔያቸውን ለመላው ዓለም የሚያስተዋውቁበት በዓል ነው።

"የአፍሪካ ቀን"  የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበትን ቀን በማስመልከት በየዓመቱ ይከበራል።

በበዓሉ አከባበር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉትየአፍሪካ ህብረት ምክትል ኮሚሽነር ካውሲ ኳሪቲ እንደገለጹት፤ በዓሉ ህብረቱ ከተመሰረተ አንስቶ ያከናወናቸውን ጠንካራ ተግባራት የሚወደስበት ነው። በተጨማሪም ለቀሩ ሥራዎች ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ቃል የምንገባበት ነው።

ህብረቱ ከምሰራታው አንስቶ እስከ አሁን የአህጉሪቷንዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት ማከናወኑን የጠቆሙት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ ለወደፊቱ በርካታ ስራዎች  እንደሚቀሩት ተናግረዋል።

ለአብነትም ስደት፣ መፈናቀል የእርስ በእርስ ጦርነት እና ድህነት አሁንም ድረስ የዜጎችን ህልውና እያስጨነቁ መሆኑን አንስተዋል።

እነዚህ ችግሮች በመፍታት ረገድ "በትኩረት ልንስራ ይገባል" በማለት ነው አጽንኦት የሰጡት።

በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ወይዘሮ ወይኒሸት ታደሰ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ አንስቶ ለህብረቱ እያበረከተች ያለውን አስተዋጽኦ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ የህብረቱ 2063 አጀንዳ በማሳካት የበለጸገች፣ የተዋሃደችና ሰላም የሰፈነባት አፍሪካን ለመፍጠር ለተቀረጸው ራዕይ እውንነት በመስራት ላይ መሆኗን ተናግረዋል።

ለአብነትም የነፃ ቪዛ፣ የቀጣናዊ ትብብር እና በሰላም ማስከበር ዘርፎች በመከናወን ላይ ያለውን ተግባር ጠቁመዋል።

በየዓመቱየአፍሪካ ቀን  መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁን የአፍሪካ ህብረት) እኤአ በ1963 መመስረቱን ተከትሎ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም