በመዲናው የግብር ገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ የደበኞች መስተንግዶ መሻሻል አሳይቷል

64

ግንቦት 16/2011 በአዲስ አበባ የግብር የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ በደበኞች መስተንግዶ መሻሻል ማሳየቱን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ተገልጋዮች ተናገሩ።
ተገልጋዮቹ የኔት ወርክ መቆራረጥ እንዲሻሻልና ወጥ የሆነ የሰራተኛ አደረጃጀትና እጥረት እንዲፈታም ጠይቀዋል።

በአዲስ አበባ በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 26 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 25 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል።

የተቋማት ሃላፊዎች በበኩላችው በዘንድሮ ዓመት በተደረገው የአሰራር ማሻሻያና የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሻለ ግብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

የኢዜአ ሪፖርተር በተለያዩ የግብር መሰብሰቢያ ጣቢያዎች ተዘዋራ ያነጋገረቻቸው ግብር ከፋዮች በሰጡት አስተያየት  ከሌሎች ዓመታት በተለየ ዘንድሮ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ማሳየቱን ገልፀዋል።

"አገልግሎት አሰጣጡ ከዚህ በፊት ከነበረው የወረፋ ብዛት የተሻለ ነው። የተሻለ አገልግሎት ነው" ያሉት አቶ ኤፍሬም ታዬ  ናቸው።

'ሲስተሙም አዲስ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ከዚህ በላይ የተሻለ ግንዛቤ ቢፈጠረም ጥሩ ነው በራሪ ወረቀትና ሌሎች ሚንሶችን ተጠቅመው የምንረዳበት ነገር ቢፈጥሩ ጥሩ ነው።'' በማለት አስተያየት የሰጡት ደረሰው ወንድም አገኘሁ  ፡፡

ግብርከፋዮቹአያይዘውምየሰራተኛ በየጊዜው መቀያየርና የሰው ሃይል እጥረት፣  የኔት ወርክ መቆራረጥና አዲስ የሚመደቡ ሰራተኞች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክፍተት እንዳለ አንስተዋል።

በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጡ የበለጠ ቀልጣፋ እንዲሆን በበሰራተኛው ዘንድ ያለው መነሳሳት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችሉ እርምጃዎችም እንዲወሰዱ መክረዋል።

መንግስት የህዝቡን ቅሬታ ለመፍታት ያደረገውን ጥረት ጥሩ ቢሆንም አገልግሎት በሚሰጥባቸውቦታዎች የኔት ወርክ መጨናናቅ እንዳይኖር መሰራት እንዳለበትም አስተያየት ሰጪዎች አሳስበዋል።

የጉለሌ ከፍለ ከተማ የሀገር ውስጥ ታክስ ጉዳዮች ሃላፊ ወይዘሮ ሙሉ ሀይለሚካኤልና የአራዳ ከፍለ ከተማ የአነስተኛግብር አወሳሰንና አሰባሰብ የስራ ሂደት ሃላፊ ወይዘሮ አገሬ ከበደ የግብር ከፋዩን ግንዛቤ በማሳደግና ከግብር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን በፍጥነት በመፍታት የተሻለ ውጤት ተገኝቷል ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም የሚነሱ ችግሮችን መሰረት በማድረግ በተወሰዱት የመፍትሄ እርምጃዎች ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል፤ በዚህም ምክንያት ከዚህ ቀደም በግብር አሰባሰብ ወቅት ይነሳ የነበረው ቅሬታ፣ የሚፈጠረው ወከባና ግርግር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።

ወይዘሮ ሙሉ እንደሚሉት ደግሞ ተቋሙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የያዘውን የገቢ መሰብሰብ እቅድ 98 በመቶ ያከናወነ ሲሆን ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ከ20 በመቶ በላይ ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።

አክለውምግብርከፋዩበግብር መክፈያ የመጨረሻ ቀን ቀደም ብሎ ግብሩን በማሳወቅ ሊፈጠር የሚችልን መጨናነቅ በመቀነስ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

የሰራተኛ እጥረት፣ የአቅም ውስንነት አልፎ አልፎ የኔት-ወርክ መቆ ራረጥና መሰል በተቋማቱ የሚታዩ ችግሮችን መፍታት እንደዚሁም ለተገልጋዩ የሚሰጠው ግብርን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር መጠናከር እንዳለበትም አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 163 ነጥብ3 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በአዲስ አበባ በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 26 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 25 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም