የግንቦት ሀያ ድሎችን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል--ዶክተር ደብረጽዮን

74

መቀሌ ግንቦት 16/2011 በግንቦት ሀያ የተገኙ ድሎች በሚገባ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ መስራት እንደሚገባ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስታዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አሳሰቡ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ በመቀሌ ከተማ በተጀመረው ሃገር አቀፍ የምክር ቤቶች የምክክር መድረክ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፣ኢትዮጰያ ላለፉት 28 ዓመታት  በሁሉም መስኮች ያስመዘገበቻቸው ድሎች የግንቦት ሃያ ውጤቶች ናቸው።

በተለይ የኢትዮጰያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ያገኟቸውን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መሰረት የተጣለው  በዚሁ የድል ቀን መሆኑን ገልጸዋል።

"ህዝቦች ለዘመናት ባካሄዱት መራር ተጋድሎ የተገኘው የግንቦት ሀያ የድል ቀን ሁሌም እንዲታወስና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ታሪኩን በሚገባ ማስተላለፍ ይገባል "ብለዋል።

ግንቦት ሀያ የሰላም፣የልማትና የዲሞክራሲ ጮራ የታየበት ዕለት እንደሆነ ያመለከቱት  ዶክተር ደብረጽዮን ይህንን ጠብቆ ለውጦቹ በወጣቱ ትውልድ ይበልጥ እንዲጠናከሩ መስራት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም