የኦሮሞና አፋር ህዝባዊ ኮንፍረንስ ተጀመረ

78

ግንቦት 16/2011 የኦሮሞና አፋር የግንኙነትና የሰላም ኮንፍረንስ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀመረ።

በኮንፍረንሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፣  የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ከሁለቱም ክልል ህዝቦች የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች ፣ ወጣቶችና ሴቶች እየተሳተፉ ነው።

የአፋርና ኦሮሞ ህዝቦች ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን የሚዳስሱ ጥናታዊ  ጽሁፎች በኮንፍረንሱ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተመራው የልዑካን ቡድን አባላት ትናንት አዳማ ከተማ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንትና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል እንደተደረገላቸው ኢዜአ ዘግቦ ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም