ለፍቼ ጨምበላላ መታሰቢያ የሩጫ ውድድሮች በሐዋሳ ይካሄዳሉ

94

ሃዋሳ ግንቦት 14 ቀን 201የፍቼ ጨምበላላበዓልንምክንያት በማድረግ በመጪው እሁድ በሐዋሳ የሩጫ ውድድሮች እንደሚካሄድ አዘጋጅ ኮሚቴው ገለጸ፡፡

ኮሚቴው የሩጫውን ዓላማና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የሩጫው አዘጋጅ አቶ ካሳሁን ካዊሶ እንደገለጹት በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለሁለተኛ ጊዜ የ10 እና የሁለት ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድሮች ይከናወናሉ፡፡በሁለት ኪሎ ሜትር ሩጫ ሕጻናት ይሳተፋሉ።

የዓለም ቅርስ የሆነውን በዓል በስፖርትመስክ በማስተዋወቅ የቱሪስት መስህብ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተጀመረው ሩጫ ቀጣይነት ኖሮት በዓሉን ለዓለም ያስተዋውቃል ብለዋል፡፡

የሩጫው ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ላሊማ ገለልቻ በበኩላቸው ሩጫው በዓሉን ከማስተዋወቅ ባለፈ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

መነሻና መድረሻውን ሱሙዳ አደባባይ በሚያደርገው ሩጫ አዋቂዎች በ10ኪሎ ሜትር፣ ህጻናት ደግሞ በሁለት ኪሎ ሜትር ሩጫ ይወዳደራሉ፡፡

በበዓሉ የሲዳማን ባህል የሚገልጹ አለባበስና ጸጉር አሰራር የሚያሳዩ እሴቶች የሚተዋወቁበት እንደሆነ የገለጹት ደግሞ የአዘጋጅ ኮሚቴው ቦርድ አባል የኔነሽ ተስፋዬ ናቸው፡፡

ውድድሩ የሲዳማን ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ መላውን ኅብረተሰብ እንደሚያሳትፍ ገልጸዋል፡፡

በሩጫው ከ30 ሺ በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ከነዚህም ታዋቂ አትሌቶችና የመንግሥት ከፍተኛ  አመራሮች ይገኙበታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም