የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ምክር ቤት የስድስት ወራት ስራ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው

56

አዲስ አበባ ግንቦት 15/2011 የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ምክር ቤት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን እየገመገመ ነው

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ በሰጡት መግለጫ፤ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚዘልቀው ግምገማ ባለፉት ስድስት ወራት የሊጉ የስራ አፈጻጸምና አገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሴቶች ሚና በሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል።

አገራዊ ለውጡ ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲጎለብት ምቹ መደላድልን የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ ሊጉ ባለፉት ስድስት ወራት ያቀዳቸውን እቅዶች ክለሳ በማድረግ በሁሉም መስኮች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲሻሻል ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

ሴቶች አገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ጠቁመው፤ ሴቶች ሰላምን በማስፈን ረገድስላላቸው ሚና አደረጃጅታቸውን በመጠቀም የንቅናቄ ስራዎች ተሰርተዋል ነው ያሉት።

በለውጡ የሴቶች ወደ ስልጣን መምጣት የራስ መተማመን ሁኔታ እንዲፈጠር መደረጉን እንደ ምቹ መደላደል ይዘን ወደታች ተንቀሳቅሰን ሰርተናል ብለዋል።

በውይይቱ አገራዊ ለወጡ ምን እድሎች፣ ፈተናዎችና መፍትሄዎች ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸው፤ እንደ ሊግ በሰላም ማረጋግጥ፣ ዴሞክራሲያዊና አቃፊ አስተሳስብ በማስፈን፣ የሴቶች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ስራዎች ላይ  ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።

ሊጉ በውስጠ ድርጅት ማጠናከር፣ የሴቶች በነጻነት እንዲያስቡ የማድረግ፣ የአባላት የማጥራትና ማብቃት እንዲሁም በኢኮኖሚና ማህበራዊ መስኮችም ተሳትፋቸው እንዲጎለበት በሚያስቸሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም