ሴት ሚኒስትሮች የሚካፈሉበት የእግር ኳስ ጨዋታ ሊደረግ ነው

104

ግንቦት 15/2011 ኢትዮጵያዊያን ሴት ሚኒስትሮች የሚካፈሉበት የእግር ኳስ ጨዋታ እንደሚካሄድ ተገለጸ። 
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ሳምንት በመጪው ሰኔ አጋማሽበሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮችለአንድ ሳምንት ያህል በተለያዩ ዝግጅት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ አረጋይ ይህን የኦሎምፒክ ሳምንት በአዲስ አበባም በተለያዩ ስፖርታዊ ፕሮግራሞች ለማክብር ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከኦሎምፒክ ሳምንቱ አንዱ ዝግጅትም የኢትዮጵያ ሴት ሚኒስትሮች ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የገዥው ፓርቲ የኢህዴግ ባለስልጣናት ከተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ጋር  የሚያደርጉት ጨዋታ  በጉጉት ከሚጠበቁ ሁነቶች መካከል ነው።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኦሎፒክ ሳምንቱ በተለያዩ ክልሎች በስፖርታዊ ውድድሮች እንደሚከበርና በአዲስ አበባ ደግሞ ፓናል ውይይትን ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል።

በዚህ የኦሎምፒክ ሳምንት ህብርተሰቡ ኮሚቴውን በገንዝብ ድጋፍ የሚያደርግበት አሰራርም የተዘረጋ በመሆኑ ህብረተሰቡ በአቅሙ ልክ ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2020 በጃፓን በሚካሄደው የዓለም የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሰፊ የቅደመ ዝግጅት ስራዎች እየተደረገ መሆኑንና ውጤት ለሚያመጡ አትሌቶችም ጠቀም ያለ የማበረታቻ ሽልማት ለመሰጠትም በሚየስችል ሁኔታ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳ ይህ የኦሎምፒክ ሳምንት ሲከበር በዋናነት የኦሎምፒክ ፍልስፍና በትክክል ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ይከናወኑበታል ብለዋል።

ስፖርት ፍቅርንና ሰላምን የሚሰብክ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ በዚህ ዓመት በሚከበረው የኦሎምፒክ ሳምንትም የህዝቡ ፍቅርና አንድነት ጎልቶ የሚሰበክበትና መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም