የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓቶችን ለአርሶ አደሩ ለማድረስ ዝግጅቱን ተጠናቋል

166

ግንቦት 15/2011 የግብርና ሚኒስቴር ለዘንድሮው የምርት ዘመን የሚውሉ የግብርና ግብዓቶችን ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። 
በምርት ዘመኑ 13 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በመሸፈን ከ406 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት ታቅዷል።

የግብርና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ለኢዜአ እንደገለጹት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የማዳበሪያ ግዥ ተፈፅሟል።

ከዚህ ውሰጥ ከ600 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይመዳበሪያ ወደ አገር ውሰጥ የገባ ሲሆን የቀረው እስከ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም አገር ውስጥ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ ዓመት ምንም አይነት የማዳበሪያ እጥረት እንደሌለ የገለጹት አቶ አለማየሁ በበቂ መጠን ተገዝቶ የገባ ሲሆን ወደብ ላይ የደረሰውምእስከ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ይገባል ተብሏል።

በኢትዮጵያ ለግብርና ልማት መዋል ከሚችለው 70 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እስካሁን መልማት የቻለው ከ16 ሚሊዮን ሄክታር አይበልጥም።

በዚህ ዓመት እንደ አፈሩ ሁኔታ ተስማሚ የሆነ 5 አይነት ማዳበሪያ መቅረቡንም  ከሃላፊው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል።

አርሶ አደሩን በበቂ ሁኔታ ሊያግዙ የሚችሉ ከ12 ሺህ በላይ የግብርና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ዝግጁ ማድርግ መቻሉንም ገልጸዋል።

በዘርፉበፓኬጆች፣ በቴክኖሎጂዎችና በአዳዲስ አሰራሮችንበመፍጠር ግብርናውን ለማዘመን ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

ፀረ ተባይና ፀር ስብል ኬሚካሎችን አርሶ አደሩ በአግባቡ እንዲጠቀምና በአካቢው ላይ ጉዳት እንዳያስከትል በባለሙያ እንዲታገዙ እየተሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።