የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ነበሩበት የማስመለሱ ተግባር ተስፋ ሰጪ ነው--- የአለም አቀፍ ድርጅቶች

76

ግንቦት  15/2011 በጉጂና ጌዴኦ ዞኖች አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ችግር የተፈናቀሉ  ዜጎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ጅምር መሆኑን የአለም አቀፉ ማህበረሰቡና የእርዳታ ድርጅቶች ተወካዮች ገለጹ፡፡

በሁለቱ ዞኖች  ዜጎችን በማፈናቀል የተጠረጠሩ ከ270 በላይ ተጠሪጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰላም ሚነስቴር አስታውቀዋል።

በአካባቢው ተጠጥለው የነበሩ  ዜጎችን ወደ ቄያቸው የመመለሱን ሂደት 15 ለሚሆኑ  የአለም አቀፍ ማህበረሰብና የእርዳታ ድርጅቶች በተመለከቱበት ወቅት እንዳሉት  በጉጂና ጌዴኦ ዞኖች ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸው ለመመለስ የሚደረገው ጥረት በጎ ጅምር ነው።

በአካባቢው በተለይም በምዕራብ ጉጂ ዞን ተዘዋውረው ባዩባቸው ቀበሌዎች ተመላሽ ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ ተሰፋ ሰጪ ቢሆንም የማስመለስ ተግባሩ ከአለም አቀፍ መስፈርት አንጻር ጥያቄዎችን አንስተዋል     

ጥያቄዎችን ካነሱት መካከል በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች የኢትዮጰያ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሳጃድ መሐመድ ሳጃድ በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ተደጋጋሚ ችግር ዜጎችን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ  መጋለጣቸውን ገልጸዋል።

“መሰል ችግሮች በቀጣይ እንዳይከሰቱ ምን ዋስተና አለ “ሲሉ ጠይቀዋል

በተለይም በማፈናቀል ሂደት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦችን ለህግ በማቅረብና  የህግ የበላይነትን በማረጋገጡ ረገድ ምን እየተሰራ እንደሆነም አንሰተዋል።

የአውሮፓ ህብረት ተወካይ ኤርክ ሃርበርስ በበኩላቸው በሁሉቱም ዞኖች ተዘዋውረው እንደተመለከቱት ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት ተሰፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

ይህም የአውሮፓ ህብረት በቀጣይ ለሚያደርገው ድጋፍ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

የተፈናቀሉ ዜጎች በጊዜያዊ መጠለያ  በነበሩበት ወቅት በተለይም ህጻናትና እናቶች ለስነ ምግብ ችግር ተጋልጠው በህክምና ከትትል ሂደት ወስጥ እንደነበሩ አስታውሰዋል።

የስነ ምግብ ችግር ያለባቸው ሆኑ በተወሳሰበ የጤና እክል ክትትል ላይ የነበሩ ዜጎች ወደ ቄያቸው ሲመለሱ ለከፋ ጉዳት እንዳይዳረጉ ያለውን  የቅድመ ዝግጅት ሰራ ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡

ሰላም  ሚኒስትር ዴኤታ ዘይኑ ጀማል በሰጡት ምላሽ እንደ ሀገር  ከሁለት ወር በፊት ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው ለመመለስ እቅድ ሲያወጡ  አለም አቀፍ መስፈርትን በጠበቁ  መልኩ እንደተፈጸመ ገልጸዋል።

እስካሁንም በጌዴኦና ጉጂ አካባቢ ከሁለቱም ወገኖች  ከ280 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ቄያቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል።

ይህም ውጤት የተገኘው መንግሥት የህግ የበላይነትን የማስከበሩ ስራን በትኩረት መስራቱን ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎችን እምነት በማሳደራቸው ነው።

በሁለቱ ዞኖች  ዜጎችን በማፈናቀል የተጠረጠሩ ከ270 በላይ ተጠሪጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።

 የህግ የበላይነት የማስከበሩ ተግባር ተጠናክሮ በመቀጠሉም በፍቃዳቸው ወደ ቄያቸው የሚመለሱ ዜጎች ቁጥር   እየጨመረ ነው።

 ችግርን በዘላቂነት ለመፍታትም  ህዝብ ለህዝብ የማቀራረቡ ተግባር በትኩረት  እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

ዜጎች ቄያቸው ሲደርሱ በመጠለያ እጦት እንዳይጎዱ 127 ሺህ ቆርቆሮና 8 ሺህ ካርቶን ምስማር ወደ አካባቢው እየደረሰ መሆኑን  ተናግረዋል።

በዘላቂነት ለማቋቋም መንግስት የሚያደርገውን ጥረት አለም አቀፍ ተቋማትና የእርዳታ ድርጅች እንዲደግፉም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም