ጫማ አምራች ኩባንያዎች ዶናልድ ትራምፕ የጀመሩትን የንግድ ጦርነት እንዲያቆሙ ጥሪ አቀረቡ

72

ግንቦት 14/2011 የአለም ትልልቅ ጫማ አምራች ኩባንያዎች የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ጋር የጀመሩትን የንግድ ጦርነት እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የንግድ ጦርነቱ ሸማቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትልም ገልፀዋል፡፡

ናይክና አዲዳስን ጨምሮ የ173 ኩባንያዎች ፊርማ ባረፈበት ደብዳቤ እንደተገለፀው ፕሬዘዳንቱ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ የ 25 % የታሪፍ ጭማሪ ውሳኔ በእጀጉ የሚጎዳ ነው ተብሏል፡፡

“አሁን ጊዜው የንግድ ጦርነቱ ማብቂያ መሆን አለበት” ሲሉም በአፅኖት ገልፀዋል፡፡

አሜሪካ ከሳምንት በፊት ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ የ 200 ቢሊዮን ዶላር የታሪፍ ጭማሪ ያደረገች ሲሆን ቻይና በበኩሏ ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ ከሰኔ ወር ጀምሮ

የ 60 ቢሊዮን ዶላር ታሪፍ ጭማሪ እንደምታደርግ ማቀዷ መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡


ምንጭ፡-ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም