በምዕራብ ኢትዮጵያ ከ137ሺህ የሚበልጡ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ተመለሱ

85

ቀምቴግንቦት 14/2011 በምዕራብ ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ግጭት ተፈናቀሉት 137ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ቄያቸው መመለሳቸውን በአሮሚያ ክልል የምሥራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤቶች አስታወቁ ፡፡
በምሥራቅ ወለጋ ዞን የነበሩ 18 የመጠለያ ካምፖች ተዘግተዋል።

ጽህፈት ቤቶቹ ለኢዜአ እንደገለጹት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ሄደዋል፡፡

የምሥራቅ ወለጋ ዞን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳርጌ ጉደታ በክልሎቹ መካከል በተፈጠረው ግጭት ከካማሺ ዞን ተፈናቅለው በአምስት ወረዳዎችና በነቀምቴ ከተማ በመጠለያ ካምፖች 68ሺህ 636 ዜጎች ወደ ቄያቸው ተመልሰዋል።

በዚህም 18 የመጠለያ ካምፖች መዘጋታቸው አስታውቀዋል፡፡

በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ ዞን 69ሺህ የሚበልጡ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለሳቸውን የዞኑ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት  አቶ ኤልያስ ከድር ተናግረዋል፡፡

ቀሪዎቹን ከ4ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በአጭር ጊዜ ውስጥ  ለመመለስ  እየተሰራ  መሆኑንም  አስታውቀዋል፡፡

ወደ ካማሺ ዞን ከተመለሱት ተፈናቃዮች መካከል የሶጌ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ አቶ ላሜሣ መኮንን በሰጡት አስተያየት የተመላሾች የቀድሞ መኖሪያ  ቤቶች  በግጭት በመውደማቸው በግለሰቦች መጋዘን ውስጥ ለመጠለል ተገደናል ብለዋል።

አቶ ገመቹ መገርሳ የተባሉ ሌላ ተፈናቃይ በበኩላቸው የቀድሞ መኖሪያቸው ጉዳት ሳይደርስበት ቢያገኙትም ፤ንብረታቸው ተዘርፎ እንዳገኙት ገልጸዋል፡፡

የበሎ ጀገንፎይ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲንሳ አመንቴ ተመላሾቹ  ማረፊያ እንዲያገኙ የተቃጠሉ መኖሪያ ቤቶችን መልሶ ለመገንባትና በርና መስኮት የሌላቸውን ቤቶች ደግሞ ጥገና እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የካማሺ ዞን ዋና እስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ኩመራ በበኩላቸው 30ሺህ ያህል ተፈናቃዮችን ተቀብለው በአምስት ወረዳዎችና በካማሺ ከተማ አስተዳደር እየሰፈሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

መኖሪያቤት ባልተዘጋጀባቸው አካባቢዎች ድንኳኖችና የፕላስቲክ ሸራዎች ለጊዜያዊ መጠለያነት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ለአርሶ አደሮችየምርትግብዓቶች ለማከፋፈልዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የቤኒሻንጉልጉምዝክልልመንግሥትየእጅናየእርሻ መሳሪያዎችን እንዲያቀርብላቸው  ጥያቄ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም