ሳውዲ አረቢያ ለሱዳን ወታደራዊ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ አደረገች

121

ግንቦት 12/2011 ሳውዲ አረቢያ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ለሚትገኘው ሱዳን 250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በሱዳን ማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ ማድረጓ ተነገረ።

በቅርብ ጊዜም ከዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ ተመሳሳይ ድጋፍ ተደርጎላት እንደነበር ይታወሳል ።

ይህ ድጋፍ  የሱዳንን የኢኮኖሚ ችግር ለማስወገድ የሚውል እንደሆነም በመረጃው ተጠቅሷል። 

ሱዳን ከገባችበት የኢኮኖሚ ቀውስ በአጭር ጊዜ ለመውጣት የተደረገላት ድጋፍ ብቸኛ መፍትሄ እንደሆነም ተዘግቧል።

ሰዎች ገንዘባቸውን ከባንከ ለማውጣት ረጃጅም ሰልፎች እየታዩ እንደደሆነና  ይህም የሆነውም አንድ ሰው ከባንክ ከ40 የአሜሪካ ዶላር  በላይ ማውጣት እንደማይችል መንግስት ገደብ ካስቀመጠ ወዲህ እንደሆነ ቢቢሰ በመረጃው አስፍሯል ።

በከተማዋ ባሉ የነዳጅ ማደያዎችም በነዳጅ እጥረት ምክንያት ሰዎች ብዙ ሰዓታትን እያባከኑ እንደሆነም ነው የተነገረው።

እአአ 2011 ደቡብ ሱዳን እንደ ሀገር ከተመሰረተች በኋላ አብዛኛው የነዳጅ ዘይት በደቡብ ሱዳን ስለሚገኝ ሱዳን በተደጋጋሚ ለኢኮኖሚ ፈተና  ተዳርጋለች።

ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር  በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለመተግበር ብሞክሩም ችግሩ ይበልጥ እንዲባባስ  እንዳደረገውም ይገለጻል።

ከፍትኛ  የሆነ ድጎማ ለደህንነት መደረጉ ጠንካራ የሆነ ሠራዊት መፍጠር እንደተቻለም ተጠቅሷል።

ከቻይና ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመመሥረት ከኳታር ድጋፍ ያገኘች ሲሆን በተመሳሳይ የዶሃ ባላንጣ ከሆነችው  ሳውዲም ድጋፍ አግኝታለች።

ባለፈው ታህሳስ ወር በምግብ እና በነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክያት በሱዳን  በተነሳው ተቃውሞ   የአልበሽር  መንግስት ባለፈው ሚያዚያ ወር መጨረሻ ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል።

በሱዳን የሽግግር መንግሥት ጉዳይ ድርድር እየተካሄደ ባለበት ወቅት በርካታ ሱዳናዊያን በአደባባይ በመውጣት ተቃውሞ በማሰማት ላይ ነበሩ።  

የቀድሞ ፕሬዝዳንት የቅርብ የጦር መሪዎች  በሳዑዲ አረቢያ በሚደረግላቸው ድጋፍ ሀገሪቷን በማስተዳደር ላይ ሲሆኑ፤ አገሪቱን ለመለወጥ ስር ነቀል ለውጥ እንደሚያስፈልጋት ተቃዋሚዎቹ እየገለፁ ይገኛሉ።   

የቀድሞ ጀኔራሎች ደግሞ ለውጡ እንዳይሳካ  የሕልም መንገድ ላይ ቆሞ ነው ያሉት  ሲል ቢቢስ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም