በግብጽ በቱሪስቶች አውቶቢስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 16 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

82

ግንቦት 12/2019 በግብፅ በብሄራዊ ሙዚየም አቅራቢያ ጊዛ ፒራሚድ አጠገብ በአንድ የቱሪስቶች አውቶቢስ ላይ በተፈፀመ ጥቃት በ16 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ከተጎዱት መካከል የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ሲገኙበት አብዛኞቹ  ቀላል ጉዳት እንዳስተናገዱና ሶስቱ  ሆስፒታል መግባታቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት  አስታውቀዋል፡፡፡

የቱሪስቶቹ አውቶብስ በሙዚየሙ አጠገብ ሲያልፍ ፍንዳታ መሰማቱን ነው ቢቢሲ ያስነበበው፡፡

ጥቃቱን እስካሁን ማን እንደፈፀመው ያልታወቀ ሲሆን  እስላማዊ ታጣቂዎች ባለፉት ጊዜያት ቱሪስቶች ላይ ጥቃት ይሰነዝሩ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል

ባለፈው ታህሳስ ወር በተፈጸመ  የመንገድ ዳር የቦንብ ጥቃት ሶስት ቱሪስት ቬትናማዊያን እና አንድ የቱሪስት ጋይድ በአውቶብስ ውስጥ እንዳሉ መገደላቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም