አካባቢን ማጽዳት ከጤና ጠቀሜታው ባሻገር ማህበራዊ ግንኙነትንም ያጠናክራል-ነዋሪዎች

135

ግንቦት 11/2011አካባቢን የማጽዳት ባህል ከጤና ጠቀሜታው ባለፈ ማህበራዊ ግንኙነት የማጠናከር ፋይዳው የላቀ መሆኑን የመቱ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የከተማው ነዋሪዎች ሀገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻውን መነሻ በማድረግ ዛሬ አካባቢያቸውን አጽድተዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ ለኢዜአ እንደገለጹት የጽዳት ዘመቻው አካባቢን ከማጽዳት ባለፈ የማህበራዊ ግንኙነታቸውን በማሳደግ በኩል አስተዋጽዎ ስላለው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በከተማውቀበሌ 01 የሚኖሩት ወይዘሮ ዘርትሁን አበራ የጽዳት ዘመቻው በንጽህና ጉድለት የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ከመከላከል ባለፈ የህብረተሰቡን የቤትና አካባቢውን የንጽህና አጠባበቅ ባህል ለማሳደግ የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል።

ስራው ቀጣይነት እንዲኖረው ህብረተሰቡ ባህል አድርጎ እንዲወስደው መንግስት ክትትል እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የኢሉአባቦር ዞን አስተዳደር እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ሺፈራው በበኩላቸው አገር አቀፉን ጥሪ ተከትሎ የተከናወነው የጽዳት ዘመቻ የአካባቢውን ንጽህና ለመጠበቅ የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል።

በጽዳት ዘመቻው የኢሉ አባቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም