ገበታ ለሸገር የእራት ምሽት ፕሮግራም ከሰዓታት በኋላ ይጀመራል

175

ግንቦት 11/2011 ገበታ ለሸገር የእራት ምሽት ከሰዓታት በኋላ መርሃ ግብሩ መካሄድ ይጀምራል።

የወጣው መርሃ ግብር እንደሚያመለክተው በዛሬው እለት ከቀኑ 9፡00 ላይ በሚደረገው የቤተ መንግሥት ጉብኝት ፕሮግራሙ ይጀመራል።

‹‹ገበታ ለሸገር›› በ29 ቢሊዮን ብር የአዲስ አበባን የወንዞች ዳርቻዎችና መናፈሻዎችን ለማልማት የተያዘ እቅድ መሆኑ ይታወቃል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ እንዳደረገው በተለያዩ ዙሮች ከ200 በላይ ግለሰቦች፣ ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ድርጅቶችና ተቋማት በዝግጅቱ ላይ ይታደማሉ።

ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶችም ድጋፍ ያደረጉበት ይህ ፕሮግራም የእራት ምሽቱ በዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ የግብር አዳራሽ እንደሚካሄድ ታውቋል።

አዲስ አበባን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም