በምስራቅ ወለጋ የወረዳ ከተሞች እግር ኳስ ክለቦች ውድድር ተጀመረ

59

 ነቀምቴ ግንቦት 10/2011 በምስራቅ ወለጋ ዞን ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የወረዳ ከተሞች የእግር ኳስ ክለቦች ውድድር ዛሬ በነቀምቴ ከተማ ተጀመረ።

ዓላማው በያቤሎ ከተማ በሚካሄደው የኦሮሚያ ከተሞች እግር ኳስ ክለቦች ውድድር ላይ ዞኑን ወክለው የሚሳተፉ ጠንካራ ስፖርተኞች ለመመልመል ነው።

እንዲሁም የወረዳ ከተሞች የስፖርት እንቅስቃሴና በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት  ለማጠናከር ጭምር እንደሆነ በመክፈቻው ስነሰርዓት ወቅት በዞኑ ስፖርት ጽህፈት ቤት የስፖርት ማስፋፊያ የስራ ሂደትመሪ       አቶ ፀጋዬ ኃይሉ ገልጸዋል።

ውድድሩ በአንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዝዮኖች ተከፍሎ እስከ ግንቦት 17/ 2011 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን እስካሁንም ከየወረዳው ከተሞች የተወከሉ 12 የእግር ኳስ ክለቦች ለውድድሩ ቀርበዋል። 

በወለጋ ስታዲዮም በተጀመረው የውድድሩ መክፈቻ ወቅት በተካሄደው ጨዋታ አንገር ጉቴ ከተማ አስተዳደር የሉጎ ከተማ አቻውን አራት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም