አቶ ወንድሙ ተክለ የአፍሪካ የሃይል እና ውሃ ኢንዱስትሪ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

55

ግንቦት 9/2011 የቀድሞው የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ድኤታ ወንድሙ ተክለ ሲጎን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ የሃይል እና ውሃ ኢንዱስትሪ ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ።

የኢትዮጵያ፣ጋና ፣ማላዊ፣ ደቡብ አፍሪካና ሩዋንዳ ፕሮጀክቶች የአፍሪካ የሃይል  እና ውሃ ኢንዱስትሪ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ኬብታዎን የተካሄደው ይህ  ዓመታዊ የአፍሪካ የሃይል እና ውሃ ኢንዱስትሪ ሽልማት ስነ ስርዓት  ጋና ግሪድ ፣ ሊሎንግዌ ዋተር ቦርድ ጨምሮ የተለያዩ ታዳሽ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በአህጉሪቱ ውስጥ በኢነርጂ እና በውሃ ኢንዱስትሪዎች ቀዳሚ ፕሮጀክቶች  በመሆን ሽልማት አግኝተዋል፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ድኤታ ወንድሙ ተክለ ሲጎ በሁለቱም ማለትም  በሃይል እና በውሃ ዘርፍ ባበረከቱት አስተዋጽኦ የህይወት ዘመን ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡


አቶ ወንድሙ 6 ሺ ሜጋ ዋት የሚያነጨው እና  60 ከመቶው ግንባታው የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያበረከቱት አስተዋፅኦ እንደ ምሳሌ ተነስቷል፡፡

አቶ ወንድሙ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በተጨማሪ ለሰባት ዓመት በስልጣን በቆዩባቸው ወቅት የተለያዩ የመሰረት ልማት ፕረጀክቶች ዲዛይን በማድረግና የገጠር ኤሌክትሮኒክስ ፕሮግራምን በማስፋፋት 6ሺ ከተሞች እና መንደሮች ተጠቃሚ በማድረግ ተሸላሚ ለመሆን ችለዋል፡፡

የቀድሞው ሚኒስትር ድኤታ በውሃ ዘርፍም የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡

የውሃ እጥረት ለመቅረፍ የድሬ የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ በቀን ያመነጭ ከነበረው 240 ሺ ሜትር ኪዩብ  ወደ 400 ሺ ሜትር ኪዩብክ ለማሳደግ ችለዋል፡፡

በሃይሉ ዘርፍ የላቀ አስተዋፅ ሽልማት አሸናፊ ደግሞ የደቡብ አፍሪካ ባዮ ተርም ኢነርጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጃሳነደራ ናይከር ናቸው፡፡

የአፍሪካ ቀዳሚ የታዳሽ ሃይል ፕሮጀክት  እንደሆነ የሚነገርለት ባዮ ተርም ኢነርጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጃሳነደራ ናይከር ፕሮጀክቱ ያመነጭ ከነበረው  4  ሜጋ ዋት ሃይል ወደ 450 ሜጋ ዋት በማሳደግ እና በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ፕሮጀክቶችን በማሸነፍ አፍሪካን ያስተሳሰሩ ዓለም አቀፍ የማዕድን ኩባንያዎች ለመሆን በማብቃታቸው ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል፡፡

በውሃ ዘርፍ የላቀ አስተዋፅ ሽልማት አሸናፊ ደግሞ በሃንጋሪ  ፓብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ልማት ጥናት ኢንስቲትዩት  የቦርድ  ፕሬዚዳንት አንድራስ ዞሎሲ ናግይ ናቸው፡፡

በስነስርዓቱ የላቀ አስተዋጽ ያበረከተ ወጣት አመራር  በሚል ዘርፍ የአስትርያ ፋታኪ  የኃይል ማመንጫ መስራች እና ፕሬዚዳንት አስትርያ ፋታኪ  አሸናፊ ሆነዋል፡፡

የዓመቱ የኃይል አገልግሎት አቅራቢ አሸናፊ ደግሞ ጋና ግሪድ ኩቡንያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው፡፡

የዓመቱ የውሃ አገልግሎት አቅራቢ አሸናፊ ደግሞ የማሊው ሊሎንግዌ ዋተር ቦርድ አሸናፊ ሆኖበታል፡፡

ከትላንት ወዲያ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የአፍሪካ የሃይል እና ውሃ ኢንዱስትሪ ሽልማት ከእነዚህ ዘርፎች በተጨማሪ በተለያዩ ዘርፎች አሸናፊ የሆኑት ተቋማት ሽልማት  እንደተበረከተላቸው አፍሪካስ ፓወር ጆርናል የተባለ ድረ-ገጽ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም