በመቀሌ ከተማ በጤና ዘርፍ ላይ ያተኮረ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

68

ግንቦት 9/2011 ከትግራይ ክልል የተወጣጡ የጤና ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ኮንፍረንስ በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በኮንፍረንሱ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ወቅት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል እንደገለጹት በክልሉ በርካታ የጤና ተቋማት የመሰረተ ልማትና የህክምና መስጪያ ቁሳቁሶች እጥረት አለባቸው።

በተቋማቱ የሚንቀሳቀሱ የጤና ባለሙያዎችም  ለስራቸው የሚመጥን ደመወዝና ጥቅማጥቅም እንደማያገኙ ተናገረል።

የጤና ተቋማትን የመሰረተ ልማትና  የባለሙያዎች የጥቅማጥቅም ችግር ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የክልሉ መንግስት የድርሻውን እንደሚወጣ ገልጸዋል።

በኮንፍረንሱ ከክልሉ 52ወረዳዎች የተውጣጡ  ከሁለት ሺህ በላይ የጤናው ዘርፍ ስራ ኃላፊዎችና  ባለሙያዎች እንዲሁም  የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎችም  የፌዴራል መንግስት አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም