ትምህርት ቤቶችና ህዘባዊ ተቋማት በህጻናት ስብዕና ግንባታ ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል-የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም

179

አዳማ  ግንቦት  8/2011   ህዝባዊ ተቋማትና ትምህርት ቤቶች በህፃናት መልካም አስተዳደግና ስብዕና ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስገነዘበ።

ተቋሙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በህፃናት መልካም አስተዳደግ፣ ስብዕና ግንባታና በጎዳ ተዳዳሪ ድጋፍ ዙሪያ ባካሄደው የቁጥጥርና የጥናት ግኝት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዳማ መክሯል።

በተቋሙ የሴቶችና ህፃናት ዕንባ ጠባቂ ወይዘሮ ሳኒያ ሳኒ እንዳለ ህዝባዊ ተቋማትና ትምህርት ቤቶች በህፃናት ስብዕና ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ በሥነ ምግባር የታነፀ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የማፍራት ኃላፊነት አለባቸው ።

ትምህርት ቤቶች እንዲሁም  የኃይማኖት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙሀንና ሌሎች ህዝባዊ ተቋማት በህጻናት ሰብዕና ግንባ ር  ቀደም ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

ተቋሙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በትምህርት ቤቶችና በህዝባዊ ተቋማት የህጻናት ስብዕና ግንባታ ላይ ያተኮረ ቁጥጥርና ጥናት ማካሄዱን አመልክተዋል።

“የጥናቱ ዓላማ ትምህርት ቤቶች ብቁና መልካም ዜጋን ከመሰረቱ ለማፍራት እንዲቻላቸው የህጻናት ስብዕና ግንባታ ባገናዘበ መልኩ ሥርዓተ ትምህርትን እንዲያሻሽሉና በሂደቱ የቤተሰብ፣ መምህራንና የተቋማትን ሚና በግልፅ ለማስቀመጥ  ነው”ብለዋል ።

ትምህርት ቤቶች የሚቀረፁ ስርዓተ ትምህርቶች ህፃናት መልካም ስብዕና ይዘው እንዲያድጉ የሚያስችሉ ሊሆኑ ይገባል

ወይዘሮ ሳኒያ አሁን በስራ ላይ ያሉ ስረዓተ ትምህርቶችንም ህዝባዊ ተቋማትን ባሳተፈና ባገናዘበ መልኩ መፈተሽና ማሻሻል እንደሚያስፈልግ  በጥናቱ መመላከቱን ጠቅሰዋል ።

የቁጥጥርና የጥናት ውጤት ለመድረኩ ያቀረቡት የተቋሙ ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ አዳነ በበኩላቸው ህዝባዊ ተቋማትና ትምህርት ቤቶች በህፃናት መልካም አስተዳደግና ስብዕና ግንባታ ላይ እየሰሩ ያሉት ተግባር አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

“ህፃናት ለአደገኛ እፅና ለመጤ ባህል እየተጋለጡ ነው” ያሉት አቶ ንጋቱ መሆናቸውን የመማር ማስተማር ሂደትን መፈተሽ፣ ምቹ የትምህርት አካባቢን መፍጠር፣የተማሪ ወላጆች፣የመምህራንና ህብረተሰቡ ግኑኝነትን ማጠናከር አን አመላክተዋል ።

“ለተግባራዊነቱ ተቋማት በቅንጅት ልንሰራ ይገባል” ብለዋል ።

መጤ ባህሎችን በማስወገድ ረገድ የቤተሰብ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ ንጋቱ አለአግባብ የሚሰርፁና የህፃናትን ስነልቦና የሚጎዱ ፕሮግራሞችና ማስተዊቂያዎች በመገኛኛ ብዙሀን እንዳይተላለፉ ተቋማቱና ብሮድካስት ባለስልጠናን በትብብር መስራት እንዳለባቸው አመላክተዋል ።

የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ፖሊሲዎችን መከለስ፣የታሪክና ሥነ ዜጋ ትምህርቶች እንዲሁም የህፃናት ክበባትና ፓርላማዎችን ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል ።

በምክክር መድረኩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከፌዴራልና ከክልል የተወጣጡ የባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም