የህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

93

ግንቦት  8/2011 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮችንና እርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ሹመትን አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ሹመቱን ያጸደቀው ዛሬ ባካሄደው 4ኛ አመት 39 መደበኛ ጉባኤው ላይ ነው።

በዚህ መሰረት ምክር ቤቱ ዶክተር ጣሰው ገብሬን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽን 

ሰብሳቢ እንዲሁም ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል።

ሹመቱ የጸደቀው በ25 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ነው።

በተመሳሳይ ምክርቤቱ ቀደም ብለው በጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ አቅራቢነት የተሾሙትን የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ የብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል እና የምክትል ሰብሳቢዋን የትነበርሽ ንጉሴን ሹመት በ4 ተቃውሞና ያለ  ድምጽ ተአቅቦ  በአብላጫ ድምጽ መርምሮ አጽድቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም