ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ ከአለም በስፋቱ ቀዳሚየሆነ ተንጠልጣይ ድልድይ አስመረቀች

102

ግንቦት 7/2011የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በናይል ወንዝ ላይ የተገነባ ከአለም በስፋቱ ቀዳሚ የሆነ ተንጠልጣይ ድልድይ ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

ድልድዩ የመሰረተ ልማት ለማሻሻል እና የስራ ዕድል ለመፍጠር በሃገሪቱ መከላከያ ከሚመሩ ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው ተብሏል፡፡

ናይልን የሚያቋርጠው ድልድዩ በስተምሥራቅ ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ግብፅ ሰሜናዊ ምዕራብ ሜዲትራኒያን የባህር ዳርቻ ድረስ የሚዘልቅና በዋና ከተማው ካይሮ የሚያጋጥመውን የመኪና መጨናነቅን ያስቀራል ተብሏል፡፡

ድልድዩ ስድስት የትራፊክ መስመሮች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ አቅጣጫ 67.3 ሜትር (222 ጫማ) ርዝመት የሚለካ ነው ተብሏል፡፡

በመክፈቻ ስነ ስርዓት የተገኙት በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ የቀጠናው ዳይሬክተር ተንጠልጣይ ድልድዩ በዓለማችን በስፋቱ ቀዳሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በግንባታው ሂደት አንድ ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ኮንክሪት፣1 ሺ 400 ብረት 160 ተንጠልጣይ ኬብሎች ጥቅም ላይ መዋላቸውን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም