የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባውን ያካሄዳል

86

ግንቦት 8/2011 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ እንደሚያካሄድ አስታወቀ።

በስብሰባውም በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ  አስታውቋል።

ኮሚቴው ለውይይት በሚቀርብ ሰነድ ላይም ከተወያየ በኋላ ቀጣይ  አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜያት ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታውሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም