የኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይና ዩኔስኮ ቅርስ ባለሙያዎች በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጥበቃ ዙሪያ ተወያዩ

254

 አዲስ  አበባ ግንቦት 7 / 2011 ከትናንት በስቲያ በተጀመረው የ2011 ሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ክለቦች ጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና በሁለተኛ ቀን ውሎው በቡድን የዙር ውድድር የተለያዩ የማጣሪያ ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡

በታዳጊ ሴቶች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌትሪክን 3 ለ 2 ኢትዮ ኤሌትሪክ የካ ክፍለ ከተማን 3 ለ 0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቁጥር ሁለትን 3 ለ 1 አሸንፈዋል።

በአዋቂ ወንዶች ኦሮሚያ ፖሊስ ማማስ ኪችንን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌትሪክን 3 ለ 2 አሸንፏል።

እንዲሁም በታዳጊ ወንዶች ኦሮሚያ ፖሊስ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3 ለ 2  ረትቷል።

በኢትዮጵያ ክለቦች የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና የዛሬ የሶስተኛ ቀን ውሎ በታዳጊ ወንዶች እና በታዳጊ ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ በአዋቂ ወንዶች የማጣሪያ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

በታዳጊ ወንዶች ኦሮሚያ ፖሊስ  ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቁጥር ሁለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮ-ኤሌትሪክ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በተጨማሪው በታዳጊ ሴቶች ኦሮሚያ ፖሊስ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቁጥር አንድ የሚጫወቱ ሲሆን፤ በአዋቂ ወንዶች ማማስ ኪችን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ይጫወታሉ።

በአጠቃላይ በሻምፒዮናው የሚያሸንፈው ክለብ ከሐምሌ 24 እስከ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ በሚካሄደው 25ኛው የአፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ክለቦች ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ እንደሚሳተፍም ከኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ፣ ማማስ ኪችን፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ እና የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር (ወወክማ) በሻምፒዮናው ላይ በሁለቱም ጾታዎች እየተሳተፉ የሚገኙ ክለቦች ናቸው።

በሻምፒዮናው ላይ 46 ወንድና 34 ሴት በድምሩ 80 ስፖርተኞች ተሳታፊ ናቸው።

የ2011 ዓ.ም ሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ የጠረጴዛ ቴኒስ ክለቦች ሻምፒዮና እስከ ግንቦት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

ከጥር 27 እስከ የካቲት 3 ቀን 2011 ዓ.ም በጅማ ከተማ በተካሄደው የ2011 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ የጠረጴዛ ቴኒስ ክለቦች ሻምፒዮና በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ አሸናፊ ነበር።

የኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይና  ዩኔስኮ ቅርስ  ባለሙያዎች በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጥበቃ ዙሪያ ተወያዩ

Reporter: Muse Melesse  awada       7/9/2011

Culture and tourism/Heritage

አዲስ  አበባ ግንቦት 7/9/2011 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ እና የባሕል ተቋም (ዩኔስኮ) ማዕቀፍ ሥር የኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይና የተቋሙ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች በላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት ጥበቃና ጥገና ዙሪያ ትናንት በፈረንሳይ ውይይት አድርገዋል

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ የባለሙያዎቹ ቡድን አብያተ ክርስቲያናቱ አሁን ያሉበትን ደረጃ ከገመገመ በኋላ በአካባቢው የሚኖረውን ህዝብ ባሳተፈ መልኩ የመፍትሄ ሀሳቦችን እንደሚያቀርብ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የፈረንሳይ መንግሥት በተለይም ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለፕሮጀክቱ ቴክኒካዊና የፋይናንስ ድጋፍ ለመስጠት ለገቡት ቃል አምባሳደር ሄኖክ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መጋቢት 3 እና 4 ቀን 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የጎበኙ ሲሆን የማክሮን የላሊበላ ጉብኝት ዓላማ ቅርሱ በአሁኑ ወቅት ያለበትን ጉዳትና ቅርሱን ከጥፋት ለመታደግ የፈረንሳይ መንግስት ሊያደርግ የሚገባውን ድጋፍ ለማጤን እንደሆነም በወቅቱ ተገልጿል። 

ፈረንሳይ በዩኔስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበውን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለማደስ የሚያስችል የገንዘብና የባለሙያ እገዛና ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷም ይታወቃል።

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፥ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ለሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ከጥፋት ለመታደግ የመነሻ የአደጋ ጊዜ የበጀት ድጋፍ አደረገ።

የበጀት ድጋፉ በፓርኩ ላይ የደረሰውን አደጋ በማጥናት ምርጥ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መሠረት ያማድረግ የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማቅረብ የኢትዮጵያ  እና ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ያካተተ ቡድን ለመቅጥር የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል።

ዩኔስኮ የበጀት ድጋፉን ያደረገው ከኢትዮጵያ መንግስት በቀረበ ጥያቄ አማካኝነት መሆኑን በፈረንሳይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።