16ኛው ዙር የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ የውጭ ምንዛሬ ማበረታቻ ሽልማት ወጣ - ኢዜአ አማርኛ
16ኛው ዙር የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ የውጭ ምንዛሬ ማበረታቻ ሽልማት ወጣ
አዲስ አበባ ግንቦት 6/2011 16 ኛው ዙር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ማበረታቻ ዕጣ በዛሬው ዕለት ለባለድለኞች ይፋ ሆነ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጠባ ባህሉን በማሳደግ በአገሪቷ የፋይናንስ ስርዓት ውስጥ ከሚያበረክተው የላቀ ድርሻ ባሻገር የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግም የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ መርሃ ግብር ዘርግቶ እየሰራበት ይገኛል።
ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ ይፋ በሆነው 16ኛው ዙር ሽልማት መሰረትም አንደኛው የቤት አውቶሞቢል የዕጣ ቁጥር 7299899 አሸናፊ ሲሆን ይህም በባንኩ በፍቼ ቅርንጫ ወጥቷል።
በሁለተኛው ዕጣ ላይ ሁለት የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎችም ለባለድለኞች የወጡ ሲሆን የአንደኛው ቁጥር የዕጣ ቁጥር 7355685 ብሔረ ጽጌ አካባቢ ቅርንጫፍ፣ ሁለተኛው የዕጣ ቁጥር 7301910 ጀሞ ቅርንጫፍ ደርሰዋል።
በተጨማሪም 16 ፍሪጆች፣ 64 ስማርት የሞባይል ቀፎዎች 3ኛና 4ኛ ዕጣ ሆነው ለባለዕድለኞች ወጥተዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ16ቱ ዙር ለባለድለኞች ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን በዕጣ አወጣጡ ወቅት ተገልጿል።
ከዚህም በተጫመሪ ባንኩ አገራዊ የቁጠባ ባህልን ለማበረታት በይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ - ግበር ብዙ ዜጎችን እንዲቆጥቡ ማስቻሉን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።