የጤና ባለሙያዎች ከጤና ሚኒስትሩ ጋር በሀዋሳ እየተወያዩ ነው

77

ሃዋሳ ግንቦት 6/2011 በደቡብ ክልል ከ1ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች ከክልሉ ርዕሰ መሰተዳድርና ከጤና ሚኒስትሩ ጋር በሀዋሳ እየተወያዩ ነው።

ዛሬ ለግማሽ ቀን የሚቆየው መድረክ በፌዴራል ደረጃ የተካሄደው ውይይት አካል መሆኑ ተነግሯል።

የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በወቅቱ እንደገለፁት መደረኩ ከጤና ባለሙያዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች መፍትሄ የሚሰጥበት ነው።

የክልልና የዞን አመራሮችም ከባለሙያዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎችን በመረዳት ምላሽ እንደሚሰጡ አመላክተዋል።

በውይይቱ የጤና ሚኒስትሩንና የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ የፌዴራልናበተለያየ ደረጃ የሚገኙ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም