የነቀምቴ ሆስፒታል 9 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የሕክምና መሣሪያዎችን በድጋፍ አገኘ

66

ነቀምቴግንቦት 2 /2011 የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ግምት ያላቸው የሕክምና መሣሪያዎችን በድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዘጠኝ ሚሊዮን የዶላር ግምት ያላቸው የሕክምና መሣሪያዎችን በድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

ሆስፒታሉ ድጋፉን ያገኘው በአሜሪካ ከሚገኘው ሜድ ሼር ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን ከተሰኘ ድርጅት ነው።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ታሪኩ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት ሆስፒታሉ በድጋፍ ያገኛቸው ለህጻናትና ለአዋቂዎች ህክምና መስጫነት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ናቸው ።

ድጋፉ በሕክምና መሣሪያዎች እጥረት የሚፈጥርበትን ችግር እንደሚቃልሉለት አስረድተው፣መሣሪያዎቹ የሆስፒታሉን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ናቸው ብለዋል።

የሆስፒታሉን ቦርድ ጨምሮ በውጭና በአገር ውስጥ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች የሆስፒታሉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል ።

በአሜሪካን የሚኖሩ የነቀምቴ ከተማና አካባቢው ተወላጆች በድጋፍ የተገኙትን  መሣሪያዎች ለማገጓጓዝ 36ሺህ300 ዶላር የትራንስፖርት ወጪ መሸፈናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል ።

የሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ዶክተር ኃይለየሱስ ተስፋዬ "መሣሪያዎቹ በዘርፉ ያለውን እጥረት ከማቃለል በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጡን ጥራት ለማሻሻል አስተዋፆ ያደርጋሉ" ብለዋል ።

የሆስፒታሉ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር ቢቂላ ነጋሣ በበኩላቸው በድጋፍ የተገኙት መሣሪያዎች ባለሙያዎች እንዲሟሉላቸይ ሲጠየቁ የነበሩና በመንግሥት አቅም ተገዝተው ሊሟሉ የማይችሉትንም እንደሚያካትቱ ተናግረዋል ።

የሆስፒታሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ድጋፉን ላደረገው ድርጅትና በውጭ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆችን አመስግነዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም