በጎ አድራጊዎች ለጌዲኦ ዞን ተፈናቃዮች 1ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

82

ግንቦት 2/2011 በጎ አድራጊዎች ለጌዲኦ ዞን ተፈናቃዮች 1.ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስና የመድኃኒት ድጋፍ አደረጉ፡፡ከድጋፍ በመጠሊያ ጣቢያዎች  ወደ ቄያቸው ለሚመለሱ ዜጎች ጠቀሜታው ጉልህ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የበጎ አድራጊዎቹ ተወካይ ዶክተር አብርሃም አስናቀ ድጋፉን ያደረጉት ተፈናቃዮቹ ያለባቸውን የጤና  ችግር ለማቃለል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ የላፍቶ ስፖርት ክበብ ሠራተኞችን በማስተባበር የተሰበሰበው ድጋፍ የህክምና ቀሳቁስ፣ የእናቶችና ህጻናት የጽዳት መጠበቂያ ዕቃዎችና መድኃኒትን ያካትታል፡፡

የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ተወካይ አቶ አክሊሉ አብርሃም በበኩላቸው በጎ ፈቃደኞቹ በራሳቸው ተነሳሽነት ላበረከቱት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ድጋፉ በስነ ምግብና በተወሳሰበ የጤና እክል የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ለሚገኙ እናቶችና ህጻናት ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይም የውሎ ገብ የህክምና አገልግሎት ክትትል እያላቸው ወደ ቄያቸው ተመላሽ ተፈናቃዮችን የግል ንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎችንና መድኃኒትእንዲያገኙ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት በአጎራባች አከባቢዎች ተከስቶ በነበረው በዚሁ ግጭት ጤና ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የተፈጠረውን የግብአትና የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት በመቅረፉ  ረገድም አስተዋፅኦ እንዳለው አብራርተዋል፡፡

ድጋፉ የተሰባሰበው ከ90 በጎነ አድራጊዎች መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም