በአዲሱ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚሰጠው የመታወቂ አሰጣጥ ቀልጣፋ አይደለም ተባለ

177

ግንቦት 2/2011 በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተዘጋጀው የመታወቂ አሰጣጥ ቀልጣፋ ባለመሆኑ ለእንግልት ተዳርገናል ሲሉ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ነዋሪዎች ገለጹ።

በአዲስ አበባ የተጀመረውና ከየካቲት 21 2011 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 10 ወረዳዎች እየተሰጠ የሚገኘው አዲሱ የዲጂታል መታወቂ ነዋሪዎችን ለእንግልት እየዳረገ ነው ተብሏል ። 

ነዋሪዎቹ አገልግሎቱን ለማግኘት ከአራት እስከ አምስት ቀን እየፈጀብን ነው ይላሉ ።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ  እንዳሉት፤ ከሳምንት በላይ ስራ ፈተው ከመጉላላት ባሻገር መታወቂያውን በወቅቱ ባለማግኘታቸው በግል ጉዳዮች ላይ ችግር እንዲገጥማቸው ምክንያት ሆኗል ።

በቀን ከ30 በለይ የሚሆኑ ሰዎች መታወቂያ ለመውሰድ ወደ ወረዳ የሚመጡ ቢሆንም አገልግሎቱን ማግኘት የሚችለው ሰው ከአምስትና ስድስት  እንደማይበልጥ ገልጸዋል።

የአዲስ  ከተማ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤፍሬም አድማሱ በበኩላቸው እንደገለጹት ፤ በ10 ወረዳዎች ላይ በዲጂታል ቴክኖለጂ የታገዘው መታወቂያ እየተሰጠ ነው ።

ይሁንና  ወረዳዎቹ የሲስተም  መቆራረጥ ችግር  እየገጠማቸው መሆኑን ገልጸው፤ በተቻለ መጠን  ለነዋሪዎች ቀልጣፋ  አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል።

ነዋሪዎቹ በአገልግሎት ሰጪውና በተገልጋዩ መሐከል ላይ ያለው የሰው ኃይል ተመጣጣኝ አለመሆኑ ጫና በማሳደሩ በተቀላጠፈ ሁኔታ ማስተናገድ እንዳይችሉ አድርጓልም ብለዋል።

 ከቅሬታ አቅራቢዎች መካከል አቶ ከበደ ካሳ እንደሉት "ሰራ ፈተን  እየተጉላላን ነው በፍጥነት እንዲሰራልን ቢደረግልን ቆንጆ ነው "

"እኔ ባለፈው ሳምንት መጥቼ ነበር የሲስተም ችግር ነበር አሉ ዛሬም ስመጣ ወረፋ ነው ያለው አሁንም ተመዝግቤ ነው የወጣሁት   ከዚህ ቀደም ከአምስትና አስር ደቂቃ በላይ አይፈጅም" የሚሉት አቶ ዮናስ ጉተም ናቸው፡፡

የአዲስ  ከተማ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤፍሬም አድማሱ እንደገለጹት ፤ በ10 ወረዳዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ  የተዘጋጀው መታወቂያ አየተሰጠ ነው ።

ከየካቲት 21 እስከ  ሚያዚያመጨረሻ በ10 ሩ ወረዳዎች 12ሺ600 መታወቂያ ለነዋሪዎች ተሰጥቷል ነው ያሉት ።

የአገልግሎቱ መጓተት የወረዳ 8 ወሳኝ ሁነትና ነዋሪዎች አገልግሎት የጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ባንቺ ጊዜ ታደሰ እንደገለጹት፤አገልግሎት አሰጣጡ ላይ  ሲጀመር ከነበረው የተሻለ ለውጥ እየታየበት ነው።

ይሁን እንጂ በድንገት የሲሰተም መቆራጥ እንደሚከሰት ገልጸው፤በቢሮው ውስጥና ከውጭ በመጡ ባለሙያዎች በመታገዝ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የባለሙያ ክፍተት መኖሩን በመግለጽ ፤የሰው ኃይል ቁጥሩን ለመጨመር   የሚመለከታቸው ኣካላት እንዲፈቱት ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። 

ኃላፊዋ በቀን ከ70 በላይ  መታወቂያዎችን  ለተገልጋይ እንዲደርሰ  እያደረግን ነውም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም