ባንኩ 'ከወለድ ነጻ' ለተሰኘው አገልግሎቱ አማካሪዎች ሰየመ

55

አዲስ አበባ ግንቦት 2/2011 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 'ከወለድ ነጻ' ለተሰኘው አገልግሎቱ የሸርዓ አማካሪዎችን ሰየመ።

ባንኩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን አምስት ግለሰቦች መሰየሙን ነው የገለጸው።

በዚሀም መሰረት ዶክተር ጄይላን ከድር የአማካሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ሼክ ሙሐመድ ሐመዲን ምክትል ሰብሳቢ፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር ኑር አብዲ፣ ዶክተር መሐመድ ዜይን እና ኡስታዝ አወል አብዱልወሃብ ደግሞ በአባልነት መሰየማቸውን በመግለጫ ጠቅሷል።

የተሰየሙት የሸርዓ አማካሪዎችም ከባንኩ ስራ አመራር አባላት ጋር ትውውቅ ማድረጋቸውና፣ ከባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ባጫ ጊና የስራ መመሪያ መቀበላቸውም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም