ባንኩ ለሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ግማሽ ቢሊዮን ብር ድጋፍ ሰጠ

87

ግንቦት 1/2011 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ግማሽ ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ባንኩ ድጋፍ ያደረገው አዲስ አበባን ጽዱና አረንጓዴ ለማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፍ ለሚያደርጉ ግለሰቦችና ተቋማት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ነው።

ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባን መልካም ገጽታ፣ ዕድገትና ለነዋሪዎቿ ምቹ አካባቢ ለመፍጠር፣ ቱሪዝምን ለማስፋፋት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ባንኩ እምነቱን ገልጿል።

ባንኩ የተለመደ ተቋማዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ግማሽ ቢሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።

ወደፊትም የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ በሚያደርጉ መሰል ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም