ኦሮሚያ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መደበ

86

ሚያዝያ 30 / 2011 በኦሮሚያ ክልል በልዩ እቅድ ለተያዘ የወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በጀት መመደቡን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ ።

የክልሉ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ልማት ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል ።

የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚህ ወቅት  እንደገለፁት የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር መፍታት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው።

"በክልሉም ሆነ በአገሪቱ የመጣው የፖለቲካ ለውጥ በኢኮኖሚ ልማት ካልተደገፈ ወጤት አይኖረውም" ያሉት አቶ ሽመልስ፣ 500ሺህ የሚሆኑ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ታቅዷል ብለዋል።

ወጣቶቹን ወደ ሥራ ለማስገባት ከተለዩ መስኮች መካከል ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ እንስሳት እርባታ፣ ማዕድን ልማት፣ ንግድ፣ አገልግሎትና አካባቢ ጥበቃ ይገኙበታል።

የመካይናዜሽንየእርሻመሳሪያዎች፣የውሃመሳቢያሞተሮች፣ዘመናዊየንብቀፎዎችናየሊዝማሽኖችን የሚያካትቱ ከ10ሺህ በላይ ቁሳቁስ ተገዝተው ለወጣቶች አንደሚቀርቡም ተናግረዋል።

"በአገሪቱ ያለው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት የሥራ አጥ ቁጥር እንዲበራከት አድርጓል" በማለት ችግሩን ያመለከቱት  አቶ ሽመልስ፤በክልሉ ያለውን ኢንቨስትመንትና ሀብት በአማራጭነት በመጠቀም ዜጎችን ወደ ሥራ ለማስገባት አቅጣጫ መያዙን አመልክተዋል።

በክልሉ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ለወጣቶች ብድር ማመቻቸት እንደሚጠበቅባቸው  ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል።

ህዝቡን የማያገለግል የመንግስትም ሆነ የግል የፋይናንስ ተቋም በክልሉ አገልግሎት መስጠት እንዳማይችል ተናግረዋል።

በህዝብ እጅ ያለውን ሀብት ማንቀሳቀስ፣ የቁጠባ ባህል ማሳደግና በፋይናንስ አሰራርን ማዘመን እቅዱን ለማሳካት በትኩረት የሚሰሩ ተግባራት መሆናቸውንም አቶ አመልክተዋል ።

ከክልሉ ከሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ700 በላይ አመራሮችና ከመንግስትና ከግል የፋይናንስ ተቋማት ተወካዮች በጉባዔው ተሳትፈዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም