የኢትዮጵያ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ በዘርፉ ችግር ፈች ጥናትና ምርምር ማድረግ አለበት-ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

59

ሚያዝያ 29/2011 ኢትዮጵያ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ በስፖርት ባለሙዎች አቅም ግንባታና በዘርፉ ችግር ፈች ጥናትና ምርምር በማድረግ የመፍትሄ  አቅጣጫ ማስቀመጥ እንዳለበት ተገለፀ።

አካዳሚው የ9ወር የእቅድ አፈጻጸም እንዲሁም በሚሻሻሉ የአካዳሚ ፖሊሲዎች ህጎችና መመሪዎች ላይ ያተኮረ የሁለት ቀን የሚቆይ ውይይት በአዳማ ጀምሯል። 

የስፖርት  ኮሚሽን  ምክትል ኮሚሽነር  አቶ ጌታቸዉ ባልቻ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ብሄራዊ ጀግና አትሌቶችንና እነሱን የሚያፈሩ ብቁ ባለያዎችን  እዲያፈራ ታልሞ የተመሰረተ ነዉ።

ከዚህም ባሻገር በዘርፉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን የመስራት ተልኮ የተሰጠዉ የስፖርት ተቋም ነዉም ብለዋል።

የስፖርት ልማት ከሳይንሳዊ  ጥናትና ምርምር ዉጭ ሊሳካ እንደማይች የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ ፤ በዚህም እየተተገበረ ያለዉ ስራ በሚፈለገዉ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግና መፍትሄ ለመስጠት የዘርፉ ባለሙዎች ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸዉ ጠቁመዋል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃብታሙ ሲሳይ በበኩላቸው አካዳሚዉ የተቋቋመበትን አላማ እንዲያሳካ መንግስት አስፈላጊዉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በስፖርቱ ልማት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት አካዳሚዉ መሬት ላይ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉና ችግር ፈች ጥናትና ምርምር ላይም ጠንክሮ መስራት እዳለበት አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶቸችና ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አንበሳዉ እንየዉ እንዳሉት አካዳሚዉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያን በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የውድድር መድረኮች ስሟን ያስጠሩና ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት ስኬታማ ተግባራትን አከናዉኗል።

ያም ቢሆን የስፖርት ባለሙዎች አቅም በመገንባትና ችግር ፈች  ጥናትና ምርምር ከማካሄድ አንፃር አካዳሚው የሚጠበቅበትን ስራ እንዳልሰራ ጠቅሰዉ  ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ሰቶ መስራት አለበት ብለዋል።

አካዳሚዉ የ9 ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርቦ ውይይት እየተካሄደበት ነዉ።

አካዳሚዉ በ2003 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በ10 የስፖርት አይነቶች በአዲስ አበባና በአሰላ እያሰለጠነ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም