የጉለሌ ክፍለ ከተማ በግልና ማህበራት ለተደራጁ 473 ወጣቶች የመስሪያ ሼዶችን አስረከበ

53

የጉለሌ ክፍለ ከተማ በግልና ማህበራት ለተደራጁ 473 ወጣቶች የመስሪያ ሼዶችን ሰርቶ ዛሬ አስረክቧል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ በግልና ማህበራት ለተደራጁ 473 ወጣቶች የመስሪያ ቦታ ሼዶችን ሰርቶ ዛሬ አስረክቧል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም አባይነህ በዚሁ ወቅት አንደገለጹት፣ ዛሬ ያስረከብነው የመስሪያ ሼዶች 473 ወጣቶችን፣ ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

መንግት በአሁኑ ወቅት ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው በተላይም ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ በስፋት እየተሰራ ነውም ብለዋል።

በዚህም በጉለሌ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታ ወይም ሼድ ያገኙት ወጣቶች  በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ተመርቀው  115 በግል 43ቱ በማህበር የተደራጁ እንደሆነም ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጥላሁን ታደሰ  በበኩላቸው፣ ከተማ አስተዳደሩ እንደ ትልቅ የቤት ስራ የያዘው ጉዳይ የወጣቱን የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

በመሆኑም በሁሉም ክፍለ ከተሞች ትልቅ ችግር የሆነውን የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ችግር ለማቃለል የከተማ አስተዳደሩ እየሰራበት ነው፤ ዛሬ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተጀመረውም የዚሁ ስራ አንዱ አካል ነው ብለዋል።

ወጣቶቹና ሴቶች እንዲሁም አካል ጉዳተኞቹም በተሰጣቸው የመስሪያ ሼዶች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በአገራቸው ሰርተው ለመኖር ይህ ትልቅ ተስፋ እንደሆነ ይናገራሉ።

በጋራ እንስራ የልብስ ስፌት ማህበር የመጡት ወይዘሮ ክብረወርቅ ወረታ የአካል ጉዳተኛ ሲሆኑ ዛሬ የመስሪያ  ሼድ ካገኙ ማህበራት መካከል ናቸው።

ለስራ ፍላጎታቸው መሳካት ይህ ዛሬ የተሰጣቸው ሼድ በብዙ እንደሚረዳቸው ገልጸው፤ መንግስት ለወጣቶችና ለአካል ጉዳተኞች በስራ ዕድል ተጠቃሚነት ላይ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በጎ ጅማሮ ነውም ብለዋል።

ሚኪያስና ጓደኞቹ የእንጨት ስራና ሰኒያና ጓደኞቿ የልብስ ስፌት ተወካይ ወጣት ሚኪያስ ሰለሞንና ወጣት ሰውዳ ሽፋ የተሰጣቸው የመስሪያ ሼድ ያሰቡትን ስራ ለመስራት ትልቁ ግብዓት እንደሚሆናቸው ገልጸዋል።

በአገር ሰርቶ ለማደግና ለመለወጥ ለሚሹት ወጣቶችም መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ በከተማዋ በሁሉም አካባቢ እድሉ ሊሰጥ ይገባልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም