የመገናኛ ብዙሃን የህዝብን አንድነት የሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ ማተኮር አለባቸው- የተለያዩ ሀገራት ጋዜጠኞች

67

አዲስ አበባ ሚየያዝያ 25/2011 ጋዜጠኞች ከወገንተኝነት ነፃ ሆነው ትክክለኛ መረጃ በማድርስ የህዝብን አንድነት የሚያጠናክር ስራ መስራት እንዳለባቸው ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ አገራት ጋዜጠኞች ገለጹ።

ጋዜጠኞች ምን ጊዜም ከወገንተኝነት ነፃ ሆነው ለህዝብ ትክክለኛ መረጃ የማድርስ ሞያዊ ግደታና ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው  የተለያዩ አገራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተናገሩ።

በአዲስ አበባ እየተከበረ ባለው 26ኛው የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን ተሳታፊ ከሆኑት ጋዜጠኞች መካከል የተወሰኑት ለኢዜአ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በአስተያየታቸውም ጋዜጠኞች ግጭቶችን ከሚፈጥሩ የጥላቻ ንግግሮችን ከማስተጋባት መቆጠብ አለባቸው።

በህዝቦች መካከል ግጭቶችን ከሚፈጥሩ የጥላቻ ንግግሮችን ከማስተጋባት መቆጠብ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

ከዩጋንዳ በመምጣት የተሳተፈው ዴቪድ ሞኮሌ እንደሚለው ጋዜጠኛ ህዝቦችን ወደ አንድነት የማምጣት ሞያዊ ሃላፊነት አለበት።

 "አንድ ጋዜጠኛ ህዝቦችን ወደ አንድነት የማምጣት ሀላፊነት አለበት ስለዚህ ምንግዜም ጋዜጠኛ ከእውነታዎች መራቅ የለበትም ከአድሎአዊነት ነጻ መሆን አለበት። ህዝቦች በጋራ ያላቸውን መልካም ነገሮች በማንሳትና መከፋፋል ሳይሆን አንድነት ያለውን ፋይዳ ማመላከት ያስፈልጋል። አንዳንዴ እኛ ጋዜጠኞች ከፋፋይ በመሆን ወደ አንድ ወገን በማድላት ግጭቶችን እናባብሳለን ግን የእኛ ሚና መሆን ያለበት አንድነትን ማጠናከር ነው። ።" 

ከዚምቧቤ ራሺዩት ሙኩንዶ "ጋዜጠኞች በህዝቦች መካካል የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታት የሚያስችሉ መረጃዎችን የማሰራጨት ሚና አላቸው ። ግጭቶች እንዳይባባሱ የማድረግ፣ የጥላቻ ንግግሮችን መጠቀም ዘርና ሌሎች ህዝቦችን የሚከፋፈሉ ጉዳዮችን ማስተጋባት የለብንም በማህበረሰባችን ያሉ መልካም ነገሮችን ማንጸባረቅ ነው ያለብን። ከተለያዩ የፓለቲካና የማህበረሰብ መሪዎች  የሚነገሩ በህዝቦች መካካል ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቃላትን ማስተጋባት የለብንም ግጭት እንዳናባብስ መጠንቀቅ አለብን ።"  ነው ያለው፡፡

ከዛምቢያ  ባዋሌ ሞታኑካም  "አንዲት አገር የሰላምና መረጋጋት እጦት ላይ በምትገኝበት ወቅት የአንድ ጋዜጠኛ ሚና መሆን ያለበት ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚያስችሉ መረጃዎችን ማስተላላፍ እውነተኛ መረጃ ማስራጨታቸውን ከአድሎ ነጻ የሆነና ግልጽ የሆነ መረጃ ማስተላላፋቸውን ማረጋጋጥ አለባቸው፡ ወቅታዊእውነተኛ መረጃን መስጠት ይጠበቅባቸዋል። "

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ማህበራት እና የሚዲያ ካውንስሎች ባለሙያዎች ስነ ምግባር በጠበቀ መልኩ እንዲሰሩ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ ተጠያቂነት የማጠናከር ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።

26ኛው የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን የተለያዩ አገራት የመገናኛ ብዙሃን ሰዎች ታድመውበት በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም