የኦሮሞና የሶማሌ ህዝቦች መቼም ቢሆን አይለያዩም---ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ

61

ሚያዝያ 23/2011 የኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦች በጊዜያዊ ችግር መቼም እንደማይለያዩ የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ አስታወቁ ።

ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ተመልሰው የተረጋጋ ኑሮ እንድመሩ የክልሉ መንግስት በሙሉ አቅም እንደሚሰራም ገልጸዋል። 

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የኦሮሞ ሕዝብ ከጭቆና አገዛዝ ለማላቀቅ ወደ ትግል የገቡትን የብሔሩን ተወላጆች የሶማሌ ሕዝብ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል።

በዚህም ትግሉ ፍሬ እንድያፈራ ማገዙን ተናግረዋል። 

"ሶማሌና ኦሮሞ በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ቤተሰብ ናቸው ፤ ግጭትና መፈናቀል የሚወገድበትና እርቅ ሰላም የሚወርድበት፣ ልማትና ለሀገር ብልፅግና በአንድነት የምንረባረብበት ወቅት ነው" ብለዋል።

ለውጡን ለመቀልበስ በኦሮሚያ ክልል ላይ ተካሄዶ የነበረው ጥቃት ተጠያቂዎቹ የቀድሞ የሶማሌ ክልል አመራሮች መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ ሙስጠፌ በወቅቱ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ለተፈፀመው አፀያፊ ተግባር በክልሉ መንግስትና ህዝብ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።

ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው የተረጋጋ ኑሮ እንድመሩ የክልሉ መንግስት በሙሉ  አቅም እንደሚሰራ አስታውቀዋል።


በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የኦሮሞና የሶማሌ ህዝቦች የወንድማማችነት የሰላም ኮንፍረንስ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ከሁለት ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም